Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 73:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

28 ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፥ መጠለያዬም ጌታ ነው ሥራህን ሁሉ እናገር ዘንድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

28 ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ ጌታ እግዚአብሔርን መጠጊያዬ አድርጌዋለሁ፤ ስለ ሥራህም ሁሉ እናገር ዘንድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

28 ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረቤ መልካም ነው፤ የአንተን ሥራ ሁሉ ለማብሠር እንድችል አንተን ጌታ አምላኬን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 73:28
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የምስጋና መሥዋዕትንም ይሠውለት፥ በእልልታም ሥራውን ይንገሩ።


ነፍሴ ሆይ፥ ወደ ዕረፍትሽ ተመለሺ፥ ጌታ መልካም አድርጎልሻልና፥


አልሞትም፥ በሕይወት እኖራለሁ እንጂ፥ የጌታንም ሥራ እናገራለሁ።


የምስኪኖችን ዕቅድ ታዛባላችሁ፥ ጌታ ግን መጠለያቸው ነው፥


ጌታን የታመነ ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።


የዓመፃ ነገር በረታብን፥ መተላለፋችንንስ አንተ ይቅር ትላለህ።


እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሁሉ፥ ኑ፥ ስሙኝ፥ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።


መዘርዘር ከምችለው በላይ ቢሆንም፥ አፌ ጽድቅህን ሁልጊዜም ማዳንህን ይናገራል።


አምላኬ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ አስተማርኸኝ፥ እስከ ዛሬም ተኣምራትህን እነግራለሁ።


ጉዳቴን የሚሹ ባፈሩና በተነወሩ ጊዜ አንደበቴ ደግሞ ሁልጊዜ ጽድቅህን ይናገራል።


አቤቱ፥ መታመናችንን እይልን፥ ወደ ቀባኸውም ፊት ተመልከት።


ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ፤ እርሱም ወደ እናንተ ይቀርባል። እናንተ ኀጢአተኞች! እጃችሁን አንጹ፤ እናንተ በሁለት ሐሳብ የምትዋልሉ ልባችሁን አጥሩ።


ክርስቶስ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዐመፀኞች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ስለ ኃጢአት መከራን ተቀበለ፤ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ሊያቀርባችሁ በሥጋ ሞተ፥ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ።


ከዚያም በኋላ ሳኦልም፥ “ፍልስጥኤማውያንን ተከትለን በሌሊት እንውረድና እስኪ ነጋ ድረስ እንዝረፋቸው፤ አንድም ሰው በሕይወት አናስቀርላቸው” አለ። እነርሱም “መልካም መስሎ የታየህን ሁሉ አድርግ” ብለው መለሱለት። ካህኑ ግን፥ “ወደ እግዚአብሔር እንቅረብ” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች