19 ስለዚህ እግዚአብሔር ሰማኝ፥ የልመናዬን ድምፅ አደመጠ።
19 አሁን ግን እግዚአብሔር በርግጥ ሰምቶኛል፤ ጸሎቴንም አድምጧል።
19 አሁን ግን በእርግጥ እግዚአብሔር ሰምቶኛል፤ የልመናዬንም ድምፅ አድምጦአል።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤
ወደ እርሱ ቅረቡ ያበራላችሁማል፥ ፊታችሁም በፍጹም አያፍርም።
ዓመፃን የምታደርጉ ሁሉ፥ ከእኔ ራቁ፥ ጌታ የልቅሶዬን ቃል ሰምቶአልና።
“በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ።