Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 65:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አንተ የመረጥኸው በአደባባዮችህም ለማደር የተቀበልኸው ምስጉን ነው፥ ከቤትህ፥ ከቅዱስ መቅደስህ፥ በረከት እንጠግባለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የመዳናችን እግዚአብሔር ሆይ፤ በጽድቅ ድንቅ አሠራር መልስልን፤ አንተ ለምድር ዳርቻ ሁሉ፣ በርቀት ላለውም ባሕር መታመኛ ነህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ጸሎታችንን ሰምተህ ድልን ታጐናጽፈናለህ፤ እኛንም ለማዳን ብዙ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ፤ ሩቅ ከሆነው ባሕር ማዶ ያሉት ሳይቀሩ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይታመናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሥራ ታዩ ዘንድ ኑ። ምክሩ ከሰው ልጆች ይልቅ ግሩም ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 65:5
28 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዐይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቅና የሚያስፈሩ ነገሮችን ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱ አምላክህ ነው።


እግዚአብሔርን እንዲህ በሉት፦ “ሥራህ እንዴት ግሩም ነው፥ ኃይልህ ብዙ ሲሆን ጠላቶች ዋሹብህ።


እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ፥ እኔ አምላክ ነኝና፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለምና ወደ እኔ ዘወር በሉ ትድኑማላችሁ።


ኃያል ሆይ፥ በግርማህና በውበትህ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ።


ችግረኞች ይበላሉ፥ ይጠግቡማል፥ ጌታንም የሚሹት ያመሰግኑታል፥ ልባቸውም ለዘለዓለም ሕያው ይሁን።


ነገር ግን እንደ ጥንካሬህና ንስሓ እንደማይገባ ልብህ የእግዚአብሔር ቅን ፍርድ በሚገለጥበት በቁጣ ቀን በራስህ ላይ ቁጣን ታከማቻለህ።


በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ያዋን፥ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።


ጽድቄ ፈጥኖ ቀርቦአል፥ ማዳኔም ወጥቶአል፥ ክንዴም በአሕዛብ ላይ ይፈርዳል፤ ደሴቶች እኔን በመተማመን ይጠባበቃሉ፥ በክንዴም ይታመናሉ።


የውሃውም መልአክ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “ያለህና የነበርህ ጌታ ሆይ! ቅዱስ ሆይ! እንዲህ ስለ ፈረድህ ጻድቅ ነህ፤


ሠረገላውንም ከኤፍሬም፥ ፈረሱንም ከኢየሩሳሌም አጠፋለሁ፤ የሰልፉም ቀስት ይሰበራል፥ ለአሕዛብም ሰላምን ይናገራል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕር፥ ከወንዙም እስከ ምድር ዳርቻ ድርስ ይሆናል።


ጌታ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርን አማልክት ሁሉ ያጠፋቸዋልና፤ የሕዝቦችም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች፥ ሁሉም በያሉበት ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


በዚያን ጊዜ የባሕሩ በረከት ወደ አንቺ ስለሚመለስ፥ የአሕዛብም ብልጽግና ወደ አንቺ ስለሚመጣ፥ አይተሽ ደስ ይልሻል፥ ልብሽም ይደነቃል ይሰፋማል።


የጌታም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።


ጌታ በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።


መዓትህንም ሁሉ አስወገድህ፥ ከቁጣህ መቅሠፍት ተመለስህ።


ወይስ በፈተና፥ በተአምራት፥ በድንቅ፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራም ኃይል፥ በዐይናችሁ ፊት ጌታ አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ፥ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?


በመርከቦች ወደ ባሕር የሚወርዱ፥ በታላላቅ ውኆች ሥራቸውን የሚሠሩ፥


ከቤትህ ሙላት ይጠግባሉ፥ ከተድላህም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ።


በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፥ ለዓለምና ለዘለዓለምም ያመሰግኑሃል።


በዚያ ቀን ይላል የሠራዊት ጌታ፥ ባርያዬ የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል ሆይ፥ እወስድሃለሁ፥ ይላል ጌታ፥ እንደ ማተሚያ ቀለበት አደርግሃለሁ፥ እኔ መርጬሃለሁና፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች