Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 64:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እግዚአብሔርም ከፍ ከፍ ይላል። ድንገተኛ ፍላጻም ያቈስላቸዋል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 በገዛ ምላሳቸው ያሰናክላቸዋል፤ ጥፋትንም ያመጣባቸዋል፤ የሚያዩአቸውም ሁሉ በትዝብት ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እግዚአብሔር ንግግራቸው በራሳቸው ላይ ተመልሶ እንዲወድቁ ያደርጋቸዋል። የሚያዩአቸው ሁሉ በፍርሃት ከእነርሱ ይሸሻሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከተ​አ​ም​ራ​ትህ የተ​ነሣ አሕ​ዛብ ይደ​ን​ግ​ጣሉ፥ በም​ድር ዳር​ቻም የሚ​ኖሩ ይፈ​ራሉ፤ በጥ​ዋት ይወ​ጣሉ፥ ማታም ይደ​ሰ​ታሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 64:8
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሚፈርድብህ አፍህ ነው እንጂ እኔ አይደለሁም፥ ከንፈሮችህም ይመሰክሩብሃል።”


አቤቱ፥ ከምኞቴ የተነሣ ለክፉዎች አትስጠኝ፥ ተንኮላቸው እንዲሳካ አትፍቀድ።


መብረቆችህን ብልጭ አድርጋቸው በትናቸውም፥ ፍላጾችህን ላካቸው አስደንግጣቸውም።


እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም፥ የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ።


ሕይወቴ በኅዘን አልቃለችና፥ ዓመታቴም በልቅሶ ጩኸት፥ ኃይሌ በችግር ደከመ፥ አጥንቶቼም ተነዋወጡ።


የሚያጠፋ ቃልን ሁሉ፥ የሽንገላ ምላስን ወደድህ።


ሕግህን እንዳይረሱ አትግደላቸው፥ አቤቱ ጋሻዬ፥ በኃይልህ በትናቸው አውርዳቸውም።


እደሰታለሁ፥ በአንተም ሐሤትን አደርጋለሁ፥ ልዑል ሆይ፥ ለስምህ እዘምራለሁ።


ክፉ ሰው በከንፈሩ ኃጢአት ይጠመዳል፥ ጻድቅ ግን ከመከራ ያመልጣል።


የሰነፍ አፍ ለራሱ ጥፋት ነው፥ ከንፈሩም ለነፍሱ ወጥመድ ነው።


ምድራቸውን ለመሣቀቂያና ለዘለዓለም ማፍዋጫ አድርገዋል፤ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፥ ራሱንም ይነቀንቃል።


ለአንተ እስራኤል መሳቂያ አልነበረምን? ወይስ ስለ እርሱ በተናገርህ ቊጥር ራስህን የምትነቀንቀው በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን?።


የሚያይሽም ሁሉ ከአንቺ ሸሽቶ፦ ነነዌ ወድማለች፤ ማን ያዝንላታል? አንቺን የሚያጽናኑ ከወዴት እፈልጋለሁ? ይላል።


“ምድሪቱ እኛንም ደግሞ እንዳትውጠን” ብለው በዙሪያቸው የነበሩ የእስራኤል ልጆች ሁሉ ከእነርሱ ጩኸት የተነሣ ሸሹ።


እነርሱም “ክፉዎችን በክፉ ሁኔታ ያጠፋቸዋል፤ የወይኑንም አትክልት ሥፍራ ፍሬውን በየጊዜው ለሚሰጡት ለሌሎች ገበሬዎች ይሰጠዋል” አሉት።


እርሱም ‘አንተ ክፉ አገልጋይ፥ አፍህ በተናገረው እፈርድብሃለሁ። እኔ ያላስቀመጥኩትን የምወስድና ያልዘራሁትን የማጭድ ጨካኝ ሰው እንደሆንሁ አወቅህ፤


ሥቃይዋንም ከመፍራት የተነሣ በሩቅ ቆመው “አንቺ ታላቂቱ ከተማ! ብርቱይቱ ከተማ ባቢሎን! ወዮልሽ! ወዮልሽ! በአንድ ሰዓት ውስጥ ፍርድሽ ይፈጸማልና፤” እያሉ ይናገራሉ።


ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኃጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርሷ ዘንድ ውጡ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች