11 ወደ ጽኑ ከተማ ማን ይወስደኛል? ማንስ እስከ ኤዶምያስ ይመራኛል?”
11 በጠላት ላይ ድልን አቀዳጀን፤ የሰው ርዳታ ከንቱ ነውና።
11 የሰው ርዳታ ከንቱ ነው። ስለዚህ ጠላቶቻችንን ድል እንድናደርግ አንተ እርዳን።
ማዳን በማይችሉ በአለቆች፥ በሰው ልጅ፥ አትታመኑ።
አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር መውጣት አቆምህ።
እርሱም እስራኤልን ከበደሉ ሁሉ ያድነዋል።
ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም፤ ፈረሶቻቸውም ሥጋ እንጂ መንፈስ አይደሉም፤ ጌታ እጁን በሚዘረጋ ጊዜ፥ ረጂው ይሰናከላል ተረጂውም ይወድቃል፥ ሁሉም በአንድ ላይ ይጠፋሉ።
የግብጽ እርዳታ ከንቱና ምንም ነው፤ ስለዚህ ስሙን፦ “በቤት የሚቀመጥ ረዓብ” ብዬ ጠርቼዋለሁ።
ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የዳዊት መዝሙር
አቤቱ፥ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው።