Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 59:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እነሆ፥ በነፍሴ ላይ አድብተዋልና፥ ብርቱዎችም በላዬ ተሰበሰቡ፥ አቤቱ፥ በበደሌም አይደለም፥ በኃጢአቴም አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እነርሱ ያለ በደሌ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተው መጡ፤ አንተ ግን ትረዳኝ ዘንድ ተነሥ፤ ሁኔታዬንም ተመልከት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ምንም በደል ሳልሠራ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተዋል፤ ይህን ተመልከትና ተነሥተህ እርዳኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ለሚ​ፈ​ሩህ ምል​ክ​ትን ሰጠ​ሃ​ቸው፥ ከቀ​ስት ፊት ያመ​ልጡ ዘንድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 59:4
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አምላኬ ጌታዬም፥ ትፈርድልኝ ዘንድ ተነሥ፥ አቤቱ፥ ፍርዴን አድምጥ።


“እግሮቻቸው ደምን ለማፍሰስ ፈጣኖች ናቸው፤


እንግዲህ አሁን እናንተ ከሸንጎው ጋር ሆናችሁ ስለ እርሱ አጥብቃችሁ እንደምትመረምሩ መስላችሁ ወደ እናንተ እንዲያወርደው ለሻለቃው አመልክቱት፤ እኛም ሳይቀርብ እንድንገድለው የተዘጋጀን ነን፤” አሉአቸው።


እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉ፥ ንጹሑን ደም ለማፍሰስ ይፈጥናሉ፤ አሳባቸው የኃጢአት አሳብ ነው፥ ጉስቁልናና ውድመት በሚሄዱበት አለ።


የጌታ ክንድ ሆይ! ተነሥ፥ ተነሥ፥ ኃይልንም ልበስ፤ በቀድሞው ወራትና በጥንቱ ዘመን በነበረው ትውልድ እንደ ሆነው ተነሥ። ረዓብን የቈራረጥህ ዘንዶውንም የወጋህ አንተ አይደለህምን?


እግሮቻቸው ወደ ክፋት ይሮጣሉና፥ ደም ለማፍሰስም ይፈጥናሉና።


ስለ አንተ ሁልጊዜ ተገድለናል፥ እንደሚታረዱም በጎች ሆነናል።


ከሐዲ ጠላቶቼ በእኔ ደስ አይበላቸው፥ በከንቱ የሚጣሉኝም በዓይናቸው አይጠቃቀሱብኝ።


በከንቱ የሚመኩ በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፥ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ።


ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት በአፈና ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት የተጣልሁት አንዳች ጥፋት ኖሮብኝ አይደለም።”


ዮናታን ለአባቱ ለሳኦል፥ ስለ ዳዊት እንዲህ ሲል መልካም ነገር ተናገረ፥ “ንጉሥ በአገልጋዩ በዳዊት ላይ ክፉ ነገር አያድርግ፤ እርሱ አልበደለህም፤ ያደረገውም ነገር በእጅጉ ጠቅሞሃል።


ይሸምቁብኛል ይሸሸጋሉ፥ ተረከዜን ይከታተላሉ፥ ነፍሴንም ለማጥፋት ይጠብቃሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች