Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 55:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 አፉ ከቅቤ ይልቅ ለዘበ፥ በልቡ ውስጥ ግን ጦርነት ነበረ፥ ቃሎቹም ከዘይት ይልቅ ለሰለሱ፥ ነገር ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የከበደህን ነገር በእግዚአብሔር ላይ ጣል፤ እርሱ ደግፎ ይይዝሃል፤ የጻድቁንም መናወጥ ከቶ አይፈቅድም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ችግርህን ሁሉ ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ እርሱም በእንክብካቤ ይጠብቅሃል፤ እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን ከቶ ለችግር አሳልፎ አይሰጣቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 55:22
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ፥ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ።


እግርህ እንዲናወጥ አይፈቅድም፥ የሚጠብቅህም አይተኛም።


ሁልጊዜ ጌታን በፊቴ አየዋለሁ፥ በቀኜ ነውና አልታወክም።


በጌታ ተስፋ አድርግ፥ በርታ፥ ልብህም ይጽና፥ በጌታ ተስፋ አድርግ።


ቢወድቅም አይጣልም፥ ጌታ እጁን ይዞ ይደግፈዋልና።


መንገድህን ለጌታ አደራ ስጥ፥ በእርሱም ታመን፥ እርሱም ያደርግልሃል።


ነፍሴ በጸጥታ እግዚአብሔርን ትጠብቅ የለምን? መድኃኒቴ ከእርሱ ዘንድ ናትና።


ነገር ግን፥ ነፍሴ ሆይ፥ እግዚአብሔርን በጸጥታ ጠብቂ፥ ተስፋዬ ከእርሱ ዘንድ ናትና።


መድኃኒቴና ክብሬ በእግዚአብሔር ነው፥ ጠንካራ ዓለቴና መጠለያዬ እግዚአብሔር ነው።


ረዳቴ ሆነኸኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ በደስታ እዘምራለሁ።


እንደ ሰይፍ ምላሳቸውን አሰሉ፥ እንደ ፍላጻ መራራ ነገርን ለመወርወር፥


ከእናንተ ጌታን የሚፈራ፥ የአገልጋዩንም ቃል የሚሰማ፥ በጨለማም የሚሄድ፥ ብርሃንም የሌለው፥ ነገር ግን በጌታ ስም የሚታመን፥ በአምላኩም የሚደገፍ ማን ነው?


ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ አቀልጣቸዋለሁ እፈትናቸዋለሁም፤ ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ክፋት ከዚህ ሌላ የማደርገው ምንድነው?


እናንተ ደካሞችና ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።


ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ስለ ነፍሳችሁ ምን እንደምትበሉና ምን እንደምትጠጡ፥ ወይም ስለ ሰውነታችሁ ምን እንደምትለብሱ አትጨነቁ፤ ነፍስ ከምግብ ሰውነትም ከልብስ አይበልጥምን?


ለደቀ መዛሙርቱም እንዲህ አለ “ስለዚህ እላችኋለሁ፤ ለነፍሳችሁ በምትበሉት ወይም ለሰውነታችሁ በምትለብሱት አትጨነቁ።


ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ተዘጋጅቶላችኋል።


እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።


እርሱ የታማኞቹን እግር ይጠብቃል ሰው በኃይሉ አይበረታምና፥ ኃጥአን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይጣላሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች