Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 44:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 ለጎረቤቶቻችን ስድብ፥ በዙሪያችንም ላሉ መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 በሕዝቦች ዘንድ መተረቻ፣ በሰዎች መካከል በንቀት ራስ መነቅነቂያ አደረግኸን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 በሕዝቦች መካከል መተረቻ አደረግኸን፤ እነርሱም ራሳቸውን ይነቀንቁብናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 በኋ​ላዋ ደና​ግ​ሉን ለን​ጉሡ ይወ​ስ​ዳሉ፥ ባል​ን​ጀ​ሮ​ች​ዋ​ንም ወደ አንተ ያቀ​ር​ባሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 44:14
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል።


ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፥ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።


ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋቸው ምድር እነቅላችኋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ አርቄ እጥለዋለሁ፥ በአሕዛብም ሁሉ መካከል ምሳሌና መሳለቂያ አደርገዋለሁ።


እኔም፦ “ያለንበትን ችግር፥ ኢያሩሳሌም እንደ ፈረሰች፥ በሮችዋም በእሳት እንደ ተቃጠሉ ታያላችሁ፤ ከእንግዲህ ወዲህ መሳለቂያ እንዳንሆን ኑና የኢየሩሳሌምን ቅጥር እንሥራ” አልኋቸው።


እኔ ደግሞ እንደ እናንተ እናገር ዘንድ ይቻለኝ ነበር፥ ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ቢሆን ኖሮ፥ እኔ በእናንተ ላይ ቃል ማሳካት፥ ራሴንም በእናንተ ላይ መነቅነቅ በተቻለኝ ነበር።


“ለሕዝብም ምሳሌ አደረገኝ፥ በፊቱ ላይ እንደሚተፉበት ሰው ሆንሁ።


እኔም በእነርሱ ዘንድ መሳለቂያ ሆንሁ፥ ሲያዩኝ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።


ማረን፥ አቤቱ፥ ማረን፥ ብዙ ንቀት አጠግቦናልና፥


እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም፥ የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ።


ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥ በዙሪያችንም ላሉ መሳቂያና መሳለቂያ።


ጌታ ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል አድርጋሃለች፥ በንቀትም ስቃብሃለች፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ስትሸሽ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።


በማሳድዳቸውም ስፍራ ሁሉ ለስድብና ለምሳሌ ለማላገጫና ለእርግማን ይሆናሉ፤ በምድርም መንግሥታት ሁሉ ዘንድ ለድንጋጤና ለክፉ ነገር አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ።


የዖምሪን ሥርዓትና የአክዓብን ቤት ሥራ ሁሉ ጠብቀሃልና፥ በምክራቸውም ሄዳችኋልና፤ ስለዚህ አንተን ለጥፋት ነዋሪዎቿን ደግሞ ለመዘባበቻ ሰጥቻችኋለሁ፥ የሕዝቤንም ስድብ ትሸከማላችሁ።


ጌታ እንድትገባ በሚያደርግበት ምድር ለአሕዛብ ሁሉ ድንጋጤ፥ መቀለጃና መዘባበቻ ትሆናለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች