Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 42:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ነፍሴ እግዚአብሔርን፥ ሕያው አምላክን ተጠማች፥ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ሰዎች ቀኑን ሙሉ፣ “አምላክህ የት አለ?” ባሉኝ ቍጥር፣ እንባዬ ቀንና ሌሊት፣ ምግብ ሆነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ቀንና ሌሊት ስለ ማልቅስ እንባዬ እንደ ምግብ ሆኖኛል፤ ጠላቶቼ “አምላክህ የት አለ?” እያሉ ዘወትር ይጠይቁኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ብር​ሃ​ን​ህ​ንና ጽድ​ቅ​ህን ላክ፤ እነ​ር​ሱም ይም​ሩኝ፥ አቤቱ ወደ መቅ​ደ​ስህ ተራ​ራና ወደ ማደ​ሪ​ያህ ይው​ሰ​ዱኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 42:3
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሕዛብ፦ “አምላካቸው ወዴት ነው?” ለምን ይበሉ፥ የፈሰሰውን የባርያዎችህን ደም በቀል በዐይኖቻችን ፊት አሕዛብ ይወቁ።


አሕዛብ፦ “አምላካቸው ወዴት ነው?” ለምን ይበሉ?


የጌታም አገልጋዮች ካህናት ከወለሉና ከመሠዊያው መካከል እያለቀሱ፦ “አቤቱ፥ ለሕዝብህ ራራ፥ አሕዛብም እንዳይነቅፉአቸው ርስትህን ለማላገጫ አሳልፈህ አትስጥ፤” ከአሕዛብ መካከል፦ “አምላካቸው ወዴት ነው?” ስለምን ይበሉ?


ጠላቶቼ ሁልጊዜ ይሰድቡኛል፥ የሚያሳድዱኝም በእኔ ስም ይራገማሉ።


የሠራዊት አምላክ አቤቱ፥ በሕዝብህ ጸሎት ላይ እስከ መቼ ትቈጣለህ?


እግዚአብሔርን፦ አንተ መጠጊያዬ ነህ፥ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ? እለዋለሁ።


ጠላቴም ታያለች፥ “ጌታ አምላክህ የት ነው?” ያለችኝን ኀፍረት ይከድናታል፥ ዐይኖቼ ያዩአታል፤ አሁን እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።


አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው።


የሚያዩኝ ሁሉ ያፌዙበኛል፥ ራሳቸውን እየነቀነቁ በከንፈሮቻቸው እንዲህ ይሳለቃሉ፦


አቤቱ፥ የሚያስጨንቁኝ ምንኛ በዙ! በኔ ላይ የሚቆሙት ብዙ ናቸው።


ጌታ ምናልባት በዚህ ቀን መከራዬን አይቶ ስለ እርግማኑ መልካም ይመልስልኛል” አላቸው።


በዓመት ሦስት ጊዜ ወንድ ሁሉ በጌታ በእግዚአብሔር ፊት ይታይ።


ከሥጋ ለባሽ ሁሉ፥ እኛ እንደ ሰማን፥ በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር የሕያው አምላክን ድምፅ ሰምቶ በሕይወቱ የኖረ ማን ነው?


አምላኬ፥ አምላኬ፥ ወደ አንተ እገሠግሣለሁ፥ ነፍሴ አንተን ተጠማች፥ ሥጋዬ አንተን እንዴት ናፈቀች በደረቅ መሬት፥ ውኃ በሌለበት በምድረ በዳ።


ነፍሴ የጌታን አደባባዮች ትወድዳለች ትናፍቅማለች፥ ልቤም ሥጋዬም በሕያው አምላክ ደስ ተሰኘ።


እጆቼን ወደ አንተ ዘረጋሁ፥ ነፍሴም እንደ ምድረ በዳ አንተን ተጠማች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች