Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 41:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፥ ጌታ በክፉ ቀን ያድነዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፤ በሕይወትም ያኖረዋል፤ በምድርም ላይ ይባርከዋል፤ ለጠላቶቹም ምኞት አሳልፎ አይሰጠውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፤ በሕይወትም ያኖራቸዋል፤ በምድር ላይ ይባርካቸዋል፤ ለጠላቶቻቸውም አሳልፎ አይሰጣቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ነፍሴ ወደ ሕያው አም​ላኬ ተጠ​ማች፤ መቼ እደ​ር​ሳ​ለሁ? የአ​ም​ላ​ኬ​ንስ ፊት መቼ አያ​ለሁ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 41:2
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሐሰት ምስክሮችና ዓመፀኞች ተነሥተውብኛልና ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ።


ሰውነትን አካላዊ እንቅስቃሴ ማለማመድ መጠነኛ ጠቀሜታ ቢኖረውም እንኳ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣውን ሕይወት የተስፋ ቃል ስላለው፥ ለሁሉ ነገር ይጠቅማል።


እርሱን የሚባርኩት ምድርን ይወርሳሉና፥ የሚረግሙት ግን ይጠፋሉ።


ነፍሳቸውን ከሞት ያድን ዘንድ፥ በራብም ጊዜ በሕይወት ይጠብቃቸው ዘንድ።


ይህን የምታደርገው የራሱ ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ሌዋዊና መጻተኛ፥ በከተሞችህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች መጥተው እንዲበሉና እንዲጠግቡ፥ አንተንም አምላክህ ጌታ በእጆችህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነው።


አማትዋም፦ “ዛሬ ከየት ቃረምሽ? ወዴትስ ሠራሽ? የተቀበለሽ የተባረከ ይሁን” አለቻት። እርሷም፦ “ዛሬ የሠራሁበት ሰው ስም ቦዔዝ ይባላል” ብላ በማን ዘንድ እንደ ሠራች ለአማቷ ነገረቻት።


ቸር ሰው ለራሱ መልካም ያደርጋል፥ ጨካኝ ግን ራሱን ይጐዳል።


ባልንጀራውን የሚንቅ ይበድላል፥ ለድሀ ግን የሚራራ ምስጉን ነው።


ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለጌታ ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።


እጅዋን ወደ ድሀ ትዘረጋለች፥ ወደ ችግረኛም እጅዋን ትሰድዳለች።


በዚያ ቀን አድንሃለሁ፥ ይላል ጌታ፤ በምትፈራቸውም ሰዎች እጅ ተላልፈህ አትሰጥም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች