12 ጠላቴ እልል አይልብኝምና በዚህም በእኔ እንደ ተደሰትክ አወቅሁ።
12 ስለ ጭንቀቴ ደግፈህ ይዘኸኛል፤ በፊትህም ለዘላለም ታኖረኛለህ።
12 ስለ ቅንነቴ እኔን ትረዳኛለህ፤ በፊትህም ለዘለዓለም ታኖረኛለህ።
ዓይኑን ከጻድቃን ላይ አያርቅም፥ ለዘለዓለምም ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፥ እነርሱም ከፍ ከፍ ይላሉ።
የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፥ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘለዓለም ፍሥሐ አለ።
እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፥ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።
አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና ፍጽምናና ቅንነት ይጠብቁኝ።
አቤቱ፥ ተቀብለኸኛልና፥ ጠላቶቼንም ደስ አላሰኘህብኝምና ከፍ ከፍ አደርግሃለሁ።
ከክፉ ነገር ሽሽ መልካምንም አድርግ፥ ሰላምን እሻ ተከተላትም።
የክፉዎች ንድ ትሰበራለችና፥ ጌታ ግን ጻድቃንን ይደግፋቸዋል።
ረዳቴ ሆነኸኛልና፥ በክንፎችህም ጥላ በደስታ እዘምራለሁ።
እግሮቼ ተሰናከሉ ባልሁ ጊዜ፥ አቤቱ፥ ጽኑ ፍቅርህ ረዳኝ።
አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር በፊት ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ፥ የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።