Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 39:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ለመዘምራን አለቃ፥ ለኤዶታም፥ የዳዊት መዝሙር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እኔ፣ “በአንደበቴ እንዳልበድል፣ መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ክፉዎችም በእኔ ዘንድ እስካሉ ድረስ፣ ልጓም በአፌ አስገባለሁ” አልሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እኔ “ድርጊቴንና አንደበቴን ከኃጢአት እጠብቃለሁ፤ በአጠገቤ ክፉ ሰው በሚገኝበት ጊዜ ሁሉ አፌን እሸብባለሁ” ብዬ ቃል ገባሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን በት​ዕ​ግ​ሥት ደጅ ጠና​ሁት፥ እር​ሱም ተመ​ልሶ ሰማኝ፥ የል​መ​ና​ዬ​ንም ቃል ሰማኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 39:1
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አፉንና ምላሱን የሚጠብቅ ነፍሱን ከመከራ ይጠብቃል።


አቤቱ፥ ለአፌ ጠባቂ አኑር፥ የከንፈሮቼንም መዝጊያ ጠብቅ።


አንደበቱን ሳይገታ፥ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።


ጎልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው።


ሕይወትን የሚመኝ ሰው ማን ነው? በጎንም ዘመን ለማየት የሚወድድ?


ስለዚህ ከሰማነው ነገር ተንሸራትተን እንዳንወድቅ፥ ለእርሱ አብልጠን ልንጠነቀቅ ይገባል።


ሞትና ሕይወት በምላስ እጅ ናቸው፥ የሚወድዱአትም ፍሬዋን ይበላሉ።


በዚህ ሁሉ ነገር ታዛዥ ብትሆንለት፥ ‘ዘሮችህ በጥንቃቄ ተጠብቀው ቢኖሩ፥ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ፥ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም’ ብሎ ጌታ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል።


ዘመኑን እየዋጃችሁ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ።


የሽንገላን ከንፈሮች ሁሉ ጌታ ያጠፋቸዋል፥ የትዕቢት ነገርን የምትናገረውን ምላስ


ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የዳዊት መዝሙር


እርሱ ግን፦ “አንቺ ከሰነፎች ሴቶች እንደ አንዲቱ ተናገርሽ፥ ከእግዚአብሔር እጅ መልካሙን ተቀበልን፥ ክፉ ነገርንስ አንቀበልምን?” አላት። በዚህ ሁሉ ኢዮብ በከንፈሩ አልበደለም።


ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የአሳፍ መዝሙር።


ኢዩ ግን ለእስራኤል አምላክ ለእግዚአብሔር ሕግ በፍጹም ልቡ ታዛዥ ሆኖ አልተገኘም፤ ይህን በማድረግ ፈንታ እስራኤልን ወደ ኃጢአት የመራቸውን የኢዮርብዓምን ክፉ አርአያነት ተከተለ።


ስለዚህ ክፉ ዘመን ነውና፥ በእንደዚህ ያለ ዘመን አስተዋይ የሆነ ሰው ዝም ይላል።


ጽኑ ፍቅሩም ለዘለዓለም ነውና ጌታን እንዲያመሰግኑ ኤማንንና ኤዶታምን፥ በስማቸውም የተጻፉትን ተመርጠው የቀሩትን ከእነርሱ ጋር በዚያ ተዋቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች