Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 38:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ጠላቶቼ ሕያዋን ናቸው ይበረቱብኝማል፥ በጠማማነትም የሚጠሉኝ በዙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 መልካሙን ስለ ተከተልሁ፣ በበጎ ፈንታ ክፉ የሚመልሱልኝ ከሰሱኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እኔ ደግ ሥራ በመሥራቴ በመልካም ፈንታ ክፉ የሚመልሱልኝ፤ በእኔ ላይ በጠላትነት ተነሥተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 38:20
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በበጎ ፈንታ ክፋትን መለሱልኝ፥ ለብቻዬም ቀረሁ።


ከክፉው እንደነበረው ወንድሙንም እንደ ገደለው እንደ ቃየል አይደለም፤ ስለምንስ ገደለው? የእርሱ ሥራ ክፉ፥ የወንድሙ ግን ጽድቅ ስለ ነበረ ነው።


ለነፍሴ ጉድጓድ ቈፍረዋልና በውኑ በመልካም ፋንታ ክፉ ይመለሳልን? ስለ እነርሱ በመልካም ለመናገር ቁጣህንም ከእነርሱ ለመመለስ በፊትህ እንደ ቆምሁ አስታውስ።


ለመልካም ነገር ቀናኢ ብትሆኑ የሚጐዳችሁ ማን ነው?


ኢየሱስ “ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ የትኛው ሥራ ትወግሩኛላችሁ?” ብሎ መለሰላቸው።


አቤቱ አምላኬ፥ እንዲህ አድርጌ ከሆነ፥ ዓመፃም በእጄ ቢኖር፥


ዳዊትም እንዲህ ብሎ ነበር፤ “ምንም ነገር እንዳይጠፋበት የዚህን ሰው ሀብት በምድረ በዳ ያን ያህል መጠበቄ ለካ በከንቱ ኖሯል፤ ደግ በሠራሁ ይኸው ክፉ መለሰልኝ።


በጎቻችንን እየጠበቅን አብረናቸው ባሳለፍነው ጊዜ ሁሉ፥ ቀንም ሆነ ሌሊት በዙሪያችን አጥር ሆነውን ነበር።


ዳዊትም፥ “የቅዒላ ነዋሪዎች እኔንና ሰዎቼን ለሳኦል አሳልፈው ይሰጡናል?” ሲል ጠየቀ። ጌታም፥ “አዎን አሳልፈው ይሰጧችኋል” አለው።


ስለዚህ ዳዊትና ሰዎቹ ወደ ቅዒላ ሄደው፥ ፍልስጥኤማውያንን ወጉ፤ እንስሶቻቸውን ማርከው ወሰዱ፤ በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ ጉዳት አደረሱ፤ ዳዊትም የቅዒላን ሕዝብ ታደገ።


ስለ ጽድቅ የሚሰደዱ ብፁዓን ናቸው፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናትና።


ጠላቶቼ እንደበዙ እይ፥ የግፍም ጥል ጠልተውኛል።


ከሐዲ ጠላቶቼ በእኔ ደስ አይበላቸው፥ በከንቱ የሚጣሉኝም በዓይናቸው አይጠቃቀሱብኝ።


እጅግ ተቸግሬአለሁና ጩኸቴን አድምጥ፥ በርትተውብኛልና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች