18 እኔስ ለመውደቅ ተቃርቤአለሁና፥ ቁስሌም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና።
18 በደሌን እናዘዛለሁ፤ ኀጢአቴም አውካኛለች።
18 በደሌን እናዘዛለሁ፤ ኃጢአቴም አስጨንቆኛል።
ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።
ኃጢአቴን ለአንተ አስታወቅሁ፥ በደሌንም አልሸፈንሁም፥ መተላለፌን ለጌታ እነግራለሁ አልሁ፥ አንተም የኃጢአቴን ሸክም ተውህልኝ።
አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ።
እርሱም በሰው ፊት እየዘመረ፦ እኔ በድያለሁ፥ ቀናውንም አጣምሜአለሁ፥ የሚገባኝንም ቅጣት አልተቀበልሁም፥
በደሌንም በውስጤ በመሸሸግ ኃጢአቴን እንደ ሰው ሰውሬ እንደሆነ፥