Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 35:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በመከራዬ ደስ የሚላቸው ይፈሩ፥ በአንድነትም ይጐስቁሉ፥ በእኔ ላይ የሚታበዩ እፍረትንና ጉስቁልናን ይልበሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 በጭንቀቴ ደስ የሚላቸው፣ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ፣ ዕፍረትንና ውርደትን ይከናነቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 በእኔ መከራ ተደስተው ትኲር ብለው በንቀት የሚመለከቱኝ ሁሉ ይፈሩ፤ ግራም ይጋቡ፤ በእኔ ላይ ራሳቸውን ከፍ ከፍ የሚያደርጉ ሁሉ ኀፍረትንና ውርደትን ይልበሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 35:26
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ በአንተ ታምኛለሁና፥ አቤቱ አምላኬ፥ አንተ ትሰማኛለህ።


ጠላቶቹንም እፍረትን አለብሳቸዋለሁ፥ በእርሱ ግን ዘውዱ ያንጸባርቃል።”


በእውነትም ብትኩራሩብኝ፥ በመዋረዴም ብታሳብቡ፥


የሚጠሉህ ኃፍረት ይከናነባሉ፥ የክፉዎችም ድንኳን አይገኝም።”


እንዲሁም እናንተ ጐልማሶች! ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም ትሕትናን እንደ ልብስ ለብሳችሁ አንዱ ሌላውን ያገልግል፤ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታኑ ግን ጸጋን ይሰጣል” ተብሎ ተጽፎአልና።


በጌታ ላይ ኰርቶአልና አስክሩት፤ ሞዓብም በጥፋቱ ላይ ይንከባለላል፥ ደግሞም መሳቂያ ይሆናል።


እነሆ፥ የሚቆጡህ ሁሉ ያፍራሉ፥ ይዋረዳሉም፤ የሚከራከሩህም እንዳልነበሩ ይሆናሉ፥ ይጠፋሉም።


ጽዮንን የሚጠሉ ሁሉ ይፈሩ፥ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።


ነፍሴን የሚቃወሙአት ይፈሩ ይጥፉም፥ ጉዳቴንም የሚፈልጉ እፍረትንና ኃሣርን ይልበሱ።


በውስጧ ጥፋት አለ፤ ተንኰልና ሽንገላ ከአደባባይዋ አይርቁም።


ነፍሴን ሊያጠፉ የሚሹ ሁሉ ይፈሩ ይጐስቁሉም፥ ክፉትን በእኔ ላይ የሚያስቡ ይዋረዱ ወደ ኋላቸውም ይመለሱ።


እንደሚለብሰው ልብስ፥ ሁልጊዜም እንደሚታጠቀው ትጥቅ ትሁነው።


ጌታ ግን እንደ አስፈሪ ተዋጊ ከእኔ ጋር ነው፤ ስለዚህ አሳዳጆቼ ይሰናከላሉ አያሸንፉም፤ አይከናወንላቸውምና በጽኑ እፍረት ያፍራሉ፥ ለዘለዓለምም በማይረሳ ውርደት ይዋረዳሉ።


ጠላቴም ታያለች፥ “ጌታ አምላክህ የት ነው?” ያለችኝን ኀፍረት ይከድናታል፥ ዐይኖቼ ያዩአታል፤ አሁን እንደ መንገድ ጭቃ ትረገጣለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች