Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 35:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ የሚከሱኝን ክሰሳቸው፥ የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚታገሉኝን ታገላቸው፤ የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔር ሆይ! የሚቃወሙኝን ተቃወማቸው፤ የሚዋጉኝንም ተዋጋቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ኀጢ​አ​ተኛ ራሱን የሚ​ያ​ስ​ት​በ​ትን ነገር ይና​ገ​ራል፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፍር​ሀት በዐ​ይ​ኖቹ ፊት የለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 35:1
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ ፍረድልኝ፥ ከጽድቅ በራቁም ሕዝብ ዘንድ ተሟገትልኝ፥ ከሸንጋይና ከግፈኛ ሰው አድነኝ።


ፍርዴን ፍረድ አድነኝም፥ ስለ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።


ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ሙግትሽን እምዋገትልሻለሁ በቀልሽንም እበቀልልሻለሁ፤ ባሕርዋንም አደርቀዋለሁ ምንጭዋንም እንዲደርቅ አደርጋለሁ።


ጌታ ግን እንዲህ ይላል፦ ከአንቺ ጋር የሚጣሉትን እጣላቸዋለሁ፥ ልጆችሽንም አድናለሁና፥ በኃያላን የተማረኩ እንኳን ይወሰዳሉ፥ የጨካኞች ብዝበዛም ቢሆን ያመልጣል።


ታዳጊአቸው ኃያል ነውና፥ እርሱም ፍርዳቸውን ከአንተ ጋር ይፋረዳልና።


ሬስ። ጌታ ሆይ፥ ስለ ነፍሴ ተምዋግተህ ሕይወቴን ተቤዠህ።


ምክንያቱም ጌታ ለእነርሱ ይሟገታልና፥ የቀሙአቸውንም ሰዎች ሕይወት ይቀማልና።


የእስራኤል ንጉሥ የወጣው በማን ላይ ነው? አንተስ የምታሳድደው ማንን ነው? የሞተ ውሻን? ወይስ ቁንጫ?


የሰረገሎቹንም ጎማ አሰረ፥ ወደ ጭንቅም አስገባቸው፤ ግብፃውያንም፦ “ጌታ ግብፃውያንን ይዋጋላቸዋልና ከእስራኤል ፊት እንሽሽ” አሉ።


ከእግዚአብሔር እንደሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም፤ በእርግጥ ከእግዚአብሔር ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ።’”


ታላቅ ጩኸትም ሆነ፤ ከፈሪሳውያንም ወገን የሆኑት ጻፎች ተነሥተው “በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይስ መልአክ ተናግሮት ይሆን?” ብለው ተከራከሩ።


በእርሱ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና፥ ጉዳዬን እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን እስኪያደርግልኝ ድረስ የጌታን ቁጣ እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቁንም አያለሁ።


የእስራኤልም አምላክ ጌታ ለእስራኤል ስለ ተዋጋላቸው ኢያሱ እነዚህን ነገሥታት ሁሉ ምድራቸውንም በአንድ ጊዜ ያዘ።


ጌታ ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ።”


አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፥ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፥ ጠላቶችህን እጠላለሁ፥ የሚቃወሙህንም እቃወማለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች