Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 34:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የአንበሳ ደቦሎች ተቸገሩ፥ ተራቡም፥ ጌታን የሚፈልጉት ግን መልካሙን ሁሉ አያጡም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፤ ስሙኝ፤ እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ልጆቼ ሆይ! ኑ አድምጡኝ፤ እኔም እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የዐ​መፃ ምስ​ክ​ሮች ተነ​ሡ​ብኝ፥ የማ​ላ​ው​ቀ​ንም በእኔ ላይ ተና​ገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 34:11
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንበሳ አደን በማጣት ይሞታል፥ የአንበሳይቱም ግልገሎች ይበተናሉ።


የተጠማችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራበችን ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና።


የጥበብ መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥ የሚያደርጓትም ሁሉ ደኅና ማስተዋልን ያገኛሉ፥ ውዳሴውም ለዘለዓለም ይኖራል።


ክብርና ሀብት በቤቱ ነው፥ ጽድቁም ለዘለዓለም ይኖራል።


የዳዊት መዝሙር። ጌታ እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።


አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፥ ዐይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።


እግዚአብሔርን የምትፈሩት ሁሉ፥ ኑ፥ ስሙኝ፥ ለነፍሴ ያደረገላትን ልንገራችሁ።


የዕውቀት መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥ ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።


ልጅን ሊሄድ በሚገባው መንገድ ምራው፥ በሸመገለም ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።


ልጆች ሆይ፥ የአባትን ተግሣጽ ስሙ፥ ማስተዋልንም ታውቁ ዘንድ አድምጡ፥


ልጆቼ ሆይ፥ አሁን እንግዲህ ስሙኝ የአፌንም ቃል አድምጡ።


እኔ የሚወድዱኝን እወድዳለሁ፥ ተግተው የሚሹኝም ያገኙኛል።


አሁንም ልጆቼ ሆይ፥ ስሙኝ፥ መንገዴንም የሚጠብቁ ምስጉኖች ናቸው።


አንተ ጐበዝ፥ በጉብዝናህ ደስ ይበልህ፥ በጉብዝናህም ወራት ልብህን ደስ ይበለው፥ በልብህም መንገድ ዐይኖችህም በሚያዩት ሂድ፥ ዳሩ ግን ስለዚህ ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ወደ ፍርድ እንዲያመጣህ እወቅ።


“እውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን?”


ልጆች ሆይ! ገና ጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፤ ትፈልጉኛላችሁ፤ ለአይሁድም ‘እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፤’ እንዳልኋቸው፥ አሁን ለእናንተ ደግሞ እላችኋለሁ።


እንዲሁም ከሕፃንነትህ አንሥቶ በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን ወደሚገኘው መዳን የሚመራህን ጥበብ ሊሰጡህ የሚያስችሉትን ቅዱስ መጻሕፍትን አውቀሃልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች