Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 32:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሁልጊዜ ከመጮኼ የተነሣ ዝም ባልሁ ጊዜ አጥንቶቼ ተበላሹ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ቀኑን ሙሉ ከመቃተቴ የተነሣ፣ ዝም ባልሁ ጊዜ፣ ዐጥንቶቼ ተበላሹ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ኃጢአቴን ሳልናዘዝ በቀረሁ ጊዜ ቀኑን ሙሉ በመቃተቴ መላ ሰውነቴ ደከመ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 አዲስ ምስ​ጋ​ና​ንም አመ​ስ​ግ​ኑት፥ በእ​ል​ል​ታም መል​ካም ዝማሬ ዘም​ሩ​ለት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 32:3
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወገቤ በትኩሳት ተሞልቷልና፥ ሥጋዬም ጤና የለውምና።


ፍላጾችህ ወግተውኛልና፥ እጅህንም በላዬ ላይ አክብደህብኛልና።


በጠራሁና በጮኽሁ ጊዜ ጸሎቴ ከለከለ።


ለመዘምራን አለቃ ስለ ንጋት ኃይል፥ የዳዊት መዝሙር።


በመኝታቸው ላይ ሆነው ያለቅሱ ነበር እንጂ በልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም፤ ስለ እህልና ስለ ወይን ጠጅ ይሰበሰቡ ነበር፤ በእኔም ላይ ዓመፁ።


ጥፋቱን የሚሰውር አይለማም፥ የሚናዘዝባትና የሚተዋት ግን ምሕረትን ያገኛል።


ቆዳዬ ጠቈረ፥ ከእኔም ተለይቶ እርግፍግፍ አለ፥ አጥንቴም ከትኩሳት የተነሣ ተቃጠለ።


እነሆ፥ እውነትን ወደድህ፥ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ።


ቤት። ሥጋዬንና ቁርበቴን አስረጀ፥ አጥንቴን ሰበረ።


ጋሜል። ይሁዳ ስለ መጨነቅና ስለ ባርነት ብዛት ተማረከች፥ በአሕዛብ መካከል ተቀመጠች ዕረፍትም አላገኘችም፥ የሚያስጨንቁአት ሁሉ ተጨንቃ አገኙአት።


ሁላችን እንደ ድቦች እንጮኻለን፤ እንደ ርግብ በመቃተት እንጮኻለን፤ ፍትህን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር እርሱ ግን የለም፤ መዳንም ከእኛ ዘንድ ርቆአል።


ልጆችሽ ዝለዋል፤ በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ በየአደባባዩ ራስ ላይ ተኝተዋል፤ በጌታ ቁጣና በአምላክሽ ተግሣጽ ተሞልተዋል።


አቤቱ፥ በቁጣህ አትቅሠፈኝ፥ በመዓትህም አትገሥጸኝ።


የሌሊቱ ስቃይ እስከ አጥንቶቼ ድረስ ይዘልቃል፥ ሁለመናዬንም ስለሚበላኝ ጅማቶቼ አያርፉም።


ከእንጀራዬ በፊት ልቅሶዬ መጥቶአልና፥ ጩኸቴም እንደ ውኃ ፈስሶአል።


የሐዘኑ ጊዜ ካበቃ በኋላም፥ ዳዊት ልኮ ቤርሳቤህን ወደ ቤቱ አስመጣት፤ ሚስቱ ሆነች፤ ወንድ ልጅም ወለደችለት፤ ነገር ግን ዳዊት የሠራው ሥራ ጌታን አላስደሰተውም ነበር።


ኃጢአት ስለ ሞላበት ስግብግብነቱ ተቈጣሁት፤ ቀጣሁት፤ ፊቴንም በቁጣ ከእርሱ ሰወርኩ፤ እርሱ ግን በመንገዱ ገፋበት።


ከዚያም ዐጥንቶቻቸውን ወስደው በኢያቢስ ባለው ታማሪስክ ተብሎ የሚጠራ ዛፍ ሥር ቀበሩ፤ ሰባት ቀንም ጾሙ።


ደስ ያላት ልብ መልካም መድኃኒት ናት፥ ያዘነች ነፍስ ግን አጥንትን ታደርቃለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች