Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ተነሥ፥ አቤቱ፥ አምላኬ ሆይ፥ አድነኝ፥ አንተ የጠላቶቼን መንጋጋ መትተሃልና፥ የክፉዎችንም ጥርስ ሰብረሃልና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን። ሴላ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 ማዳን የእግዚአብሔር ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፥ በረከትህ በሕዝብህ ላይ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ማዳን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ በረ​ከ​ት​ህም በሕ​ዝ​ብህ ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 3:8
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔ፥ እኔ ጌታ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም የሚያድን የለም።


ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።


እኔ ግን ጌታ፥ ከግብጽ ምድር ጀምሬ አምላክህ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም፥ ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ የለም።


በታላቅም ድምፅ እየጮሁ “ማዳን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው የአምላካችንና የበጉ ነው!” አሉ።


በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በሰማያዊ ስፍራ በክርስቶስ የባረከን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ።


መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”


ፈረስ ለጦርነት ቀን ይዘጋጃል፥ ድል ግን ከጌታ ዘንድ ነው።


ለእናንተ አስቀድሞ እግዚአብሔር ብላቴናውን አስነሥቶ፥ እያንዳንዳችሁን ከክፋታችሁ እየመለሰ ይባርካችሁ ዘንድ ላከው።”


ስሙ ለዘለዓለም ይታወስ፥ እንደ ፀሐይ ዕድሜ ስሙ ጸንቶ ይኑር፥ የምድር አሕዛብ ሁሉ በርሱ ይባረኩ፥ አሕዛብ ሁሉ ያመሰግኑት፥


በእውነት ኮረብቶች ሐሰት ናቸው፥ በተራሮችም ላይ ሁከት ነው፤ በእውነት የእስራኤል መዳን በአምላካችን በጌታ ነው።”


ከዚህ በኋላ በሰማይ የብዙ ሕዝብ ታላቅ ድምፅን የመሰለ ድምፅ ሰማሁ፦ “ሃሌ ሉያ! ማዳንና ክብር ኃይልም የአምላካችን ነው፤”


ጌታ ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፥ ጌታ ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።


ክፉን በክፉ ወይም ስድብን በስድብ ፈንታ አትመልሱ፤ በዚህ ፈንታ ባርኩ፤ ምክንያቱም በረከትን ልትወርሱ ተጠርታችኋል።


እንዲህ ሲል፥ “በእውነት መባረክን እባርክሃለሁ፤ ማብዛትንም አበዛሃለሁ፤”


ሙሴም ታቦቱ በተጓዘ ጊዜ ሁሉ እንዲህ ይል ነበር፦ “አቤቱ፥ ተነሣ፥ ጠላቶችህም ይበተኑ፥ የሚጠሉህም ከፊትህ ይሽሹ።”


ሻማ ግን የቆመበትን ስፍራ አለቀቀም፤ ጦርነቱንም ተቋቁሞ ፍልስጥኤማውያንን ገደለ፤ በዚያችም ዕለት ጌታ ታላቅ ድልን አደረገ።


አቤቱ፥ ተነሣ፥ ሰውም አይበርታ፥ አሕዛብም በፊትህ ይፈረድባቸው።


ርስቴ በእጅህ ነው፥ ከጠላቶቼ እጅና ከሚያሳድዱኝ አድነኝ።


አምላክ ሆይ ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ስበር፥ የአንበሶቹን መንጋጋቸውን አድቅቅ።


እኔ የአንተ ነኝ፥ ፍርድህን ፈልጌአለሁና አድነኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች