Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 29:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጌታ የጥፋት ውኃን ሰብስቦአል፥ ጌታ ለዘለዓለም ንጉሥ ሆኖ ይቀመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እግዚአብሔር በጐርፍ ላይ ዙፋኑን ዘርግቶ ተቀምጧል፤ እግዚአብሔር በንጉሥነቱ ለዘላለም በዙፋኑ ላይ ይቀመጣል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እግዚአብሔር የጥልቁ ባሕር ገዢ ነው፤ በንጉሥነቱም ለዘለዓለም ይገዛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰማ፥ ይቅ​ርም አለኝ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ረዳቴ ሆነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 29:10
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ ለዘለዓለም ንጉሥ ነው፥ አሕዛብ ከምድሩ ይጠፋሉ።


እነሆ፥ እኔ ከሰማይ በታች የሕይወት እስትንፋስ ያለውን ሥጋ ሁሉ ለማጥፋት፥ በምድር ላይ የጥፋት ውኃን አመጣለሁ፥ በምድር ያለ ሁሉ ይጠፋል።


ለዘመናትም ንጉሥ፥ ለማይሞተው፥ ለማይታየው፥ ብቻውን አምላክ ለሆነው መፈራትና ክብር ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን! አሜን።


እጅግም ፈሩና “እንዲህ ነፋስም ባሕርም የሚታዘዙለት ይህ ማን ነው?” ተባባሉ።


ከክፉ አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን።’


ጌታ ነገሠ፥ አሕዛብ ይደንግጡ፥ በኪሩቤል ላይ ተቀመጠ፥ ምድር ትናወጥ።


ጌታ ነገሠ፥ ግርማን ተጐናጸፈ፥ ጌታ ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፥ ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት።


በጉልበትህ ተራሮችን አጸናሃቸው፥ በኃይልም ታጥቀሃል።


የጌታ ድምፅ በውኆች ላይ፥ የክብር አምላክ አንጐደጐደ፥ አምላክ በብዙ ውኆች ላይ።


ባድማውንና ውድማውን እንዲያጠግብ፥


ጌታ ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ ዙፋኑንም ለመፍረድ አዘጋጀ፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች