Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 28:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የዳዊት መዝሙር። አቤቱ፥ ወደ አንተ እጠራለሁ፥ ዝም ብትለኝ ወደ ጉድጓድ እንደሚወርዱት እንዳልመስል፥ አንተ ዓለቴ ሆይ፥ ዝም አትበለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 እግዚአብሔር ሆይ፤ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ ዐለቴ ሆይ፤ ሰምተህ እንዳልሰማ አትሁንብኝ፤ አንተ ዝም ካልኸኝ፤ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ እሆናለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 መከታዬ እግዚአብሔር ሆይ! ወደ አንተ ስጣራ ጩኸቴን ስማ! አንተ ካልሰማኸኝ ግን ወደ መቃብር ከሚወርዱት እንደ አንዱ መሆኔ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የአ​ማ​ል​ክት ልጆች ሆይ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥ የጊ​ደ​ሮ​ችን ጥጃ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ። ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አምጡ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 28:1
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ነፍሴ ወደ መቃብር እንዳትወርድ አድኖአታል፥ ሕይወቴም ብርሃንን ታያለች ይላል።”


ጸሎት፥ በዋሻ በነበረ ጊዜ፥ የዳዊት ትምህርት።


በሙሉ ድምጼ ወደ ጌታ ጮኽሁ፥ በሙሉ ድምጼ ወደ ጌታ ለመንሁ።


አቤቱ፥ ፈጥነህ ስማኝ፥ መንፈሴ ዛለ፥ ፊትህን ከኔ አትሰውር፥ ወደ ጉድጓድም እንደሚወርዱ እንዳልሆን።


እንዲህም አለ፦ አቤቱ ጉልበቴ ሆይ፥ እወድድሃለሁ።


አምላኬ፥ አምላኬ፥ ለምን ተውኸኝ? እኔን ከማዳንና ከጩኸቴ ለምን ራቅህ?


አንተ ግን፥ አቤቱ፥ ጋሻዬ ነህ፥ ክብሬና ራሴንም ቀና የምታደርገው አንተ ነህ።


አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት፥ ወደ ጉድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።


አቤቱ፥ ወደ አንተ ጠራሁ፥ ወደ አምላኬም ለመንሁ።


አቤቱ፥ አንተ አየኸው፥ ዝም አትበል፥ አቤቱ፥ ከእኔ አትራቅ።


በተግሣጽህ ስለ ኃጢአቱ ሰውን ዘለፍኸው፥ የሚመኘውንም እንደ ብል ታጠፋበታለህ፥ በእውነት ሰው ሁሉ ከንቱ ነው።


ጌታ በቀን ቸርነቱን ያዝዛል፥ በሌሊትም ዝማሬው በእኔ ዘንድ ይሆናል፥ የእኔ ስእለት ለሕይወቴ አምላክ ነው።


አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥ መቃተቴንም አስተውል፥


እንዳይውጠኝ ከረግረግ አውጣኝ፥ ከሚጠሉኝና ከጥልቅ ውኃ አስጥለኝ።


ለመዘምራን አለቃ፥ ስለ ኤዶታም፥ የአሳፍ መዝሙር።


የአሳፍ የምስጋና መዝሙር።


“በሙሉ ሕይወት እያሉ፥ ከነነፍሳቸው፥ እንደ ሲኦል ሆነን እንዋጣቸው፥ ወደ ጉድጓድ እንደሚወድቁም ይሁኑ፥


ጌታ እግዚአብሔር የዘለዓለም ዐለት ነውና ለዘለዓለም በጌታ ታመኑ።


ሲኦል አያመሰግንህምና፥ ሞትም አያከብርህምና፤ ወደ ጉድጓዱ የሚወርዱ እውነትህን ተስፋ አያደርጉም።


ሺህ ዓመትም አሰረው፤ ወደ ጥልቅም ጣለው፤ አሕዛብንም ወደ ፊት እንዳያስት ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ በእርሱ ላይ ዘግቶ ማኅተም አደረገበት፤ ከዚያም በኋላ ለጥቂት ጊዜ መፈታት ይገባዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች