Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 27:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 አቤቱ፥ መንገድህን አስተምረኝ፥ በጠላቶቼም ምክንያት በቀና መንገድ ምራኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔር ሆይ፤ መንገድህን አስተምረኝ፤ ስለ ጠላቶቼም፣ በቀና መንገድ ምራኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እግዚአብሔር ሆይ! የምመራበትን መንገድ አስተምረኝ፤ በጠላቶቼም ምክንያት በተደላደለ መንገድ ምራኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 27:11
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔ ግን በቸርነትህ ብዛት ወደ ቤትህ እገባለሁ፥ አንተን በመፍራት ወደ ቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ።


አቤቱ፥ መንገድህን ምራኝ፥ በእውነትህም እሄዳለሁ፥ ስምህን ለመፍራት ልቤ ደስ ይለዋል።


እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፥ አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።


በፍጹም ልቤ ፈለግሁህ፥ ከትእዛዝህ አታርቀኝ።


ለእነርሱ ለራሳቸው ክፉ ነገርን አጸኑ፥ ወጥመድን ይሰውሩ ዘንድ ተማከሩ፥ ማንስ ያየናል? ይላሉ።


በዚያም አውራ ጎዳና ይኖራል፥ እርሱም የተቀደሰ መንገድ ይባላል፤ ንጹሐን ያልሆኑ አያልፉበትም፥ የእርሱ የሆኑ ሕዝቦች ግን ያልፉበታል፤ ተጓዦች ሆኑ፥ ሰነፎች እንኳ አይስቱበትም።


የብዙ ሰዎችን የክፋት ሹክሹክታ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፦ “ምናልባት ይታለል እንደሆነ፥ እናሸንፈውም እንደሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን” ይላሉ።


ትሑታንን በፍርድ ይመራል፥ ለትሑታን መንገድን ያስተምራቸዋል።


በቅርብ እየተከታተሉትም ለገዢው ግዛትና ሥልጣን አሳልፈው እንዲሰጡት ጻድቃን መስለው በቃሉ የሚያጠምዱትን ሰላዮች ላኩበት።


እነርሱ ለሚያስተውል የቀኑ ናቸው፥ እውቀትንም ላገኟት ትክክል ናቸው።


ጌታን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ እርሱን ያስተምረዋል።


የታካች መንገድ እንደ እሾህ አጥር ናት፥ የጻድቃን መንገድ ግን የተደላደለች ናት።


እንግዶች ተነሥተውብኛልና፥ ጨካኞችም ነፍሴን ሽተዋታልና። እግዚአብሔርን በፊታቸው አላደረጉትም።


አቤቱ፥ በጠላቶቼ ምክንያት በጽድቅህ ምራኝ፥ መንገዴን በፊትህ አቅና።


በደልንም በእኔ ውስጥ ብታገኝ እይ፥ የዘለዓለምንም መንገድ ምራኝ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች