Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 22:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 በታላቅ ጉባኤ ምስጋናዬ ከአንተ ዘንድ ነው። እርሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እሰጣለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ምስኪኖች በልተው ይጠግባሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹትም ያመሰግኑታል፤ ልባችሁም ለዘላለም ሕያው ይሁን!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ድኾች እስኪጠግቡ ይበላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹት ያመሰግኑታል፤ ልባቸው በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ይደሰታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 22:26
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቀንድና ሰኰና ካበቀለ ኰርማ ወይም ወይፈን ይልቅ ጌታን ደስ ያሰኘዋል።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አገልጋዮቼ ይበላሉ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ እነሆ፥ አገልጋዮቼ ይጠጣሉ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ እነሆ፥ አገልጋዮቼ ደስ ይላቸዋል እናንተ ግን ታፍራላችሁ፤


እሰይ እሰይ የሚሉኝ እፍረታቸውን ወዲያው ይከፈሉ።


የሠራዊት ጌታም ለሕዝብ ሁሉ በዚህ ተራራ ላይ ታላቅ የሰባ ግብዣ፥ ያረጀ የወይን ጠጅ፥ ቅልጥም የሞላባቸው የሰቡ ነገሮች፥ መልካምና የበሰለ የወይን ጠጅ ግብዣ ያደርጋል።


እኔ ከምሰጠው ውሃ የሚጠጣ ሁሉ ግን ለዘለዓለም አይጠማም፤ እኔ የምሰጠው ውሃ በእርሱ ውስጥ ለዘለዓለም ሕይወት የሚፈልቅ የውሃ ምንጭ ይሆናል እንጂ፤” አላት።


የተጠማችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራበችን ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና።


ዳዊትም በጉባኤው ሁሉ ፊት ጌታን ባረከ፤ ዳዊትም እንዲህ አለ፦ “አቤቱ፥ የአባታችን የእስራኤል አምላክ ሆይ! ከዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ተባረክ።


በታላቅ ጉባኤ ጽድቅን አበሠርሁ፥ እነሆ፥ ከንፈሮቼን አላግድም፥ አቤቱ፥ አንተ ታውቃለህ።


ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ሠዋ፥ ለልዑልም ስእለትህን ስጥ፥


በሕዝቡ ሁሉ ፊት፥ እነሆ ስእለቴን ለጌታ እፈጽማለሁ።


በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለጌታ እፈጽማለሁ፥


እኔ ግን ከምስጋና ቃል ጋር እሠዋልሃለሁ፤ የተሳልሁትንም እፈፅማለሁ። ደኅንነት ከጌታ ነውና።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች