Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 22:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ጭንቀት ቀርባለችና የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ብዙ ኰርማዎች ከበቡኝ፤ ኀይለኛ የባሳን በሬዎችም ዙሪያዬን ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 ብዙ ጠላቶች እንደሚዋጉ በሬዎች ከበውኛል፤ እንደ ባሳን ተዋጊ ኰርማዎችም በዙሪያዬ ናቸው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 22:12
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በኢየሩሳሌም ስላለው መቅደስህ ነገሥታት እጅ መንሻን ለአንተ ያመጣሉ።


በቀባኸው በቅዱሱ ብላቴናህ በኢየሱስ ላይ ሄሮድስና ጴንጤናዊው ጲላጦስ ከአሕዛብና ከእስራኤል ሕዝብ ጋር፥ እጅህና አሳብህ እንዲሆን አስቀድመው የወሰኑትን ሁሉ ሊፈጽሙ፥ በዚች ከተማ በእውነት ተሰበሰቡ።


በነጋም ጊዜ ሊቃነ ካህናትና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ሁሉ ኢየሱስን ሊገድሉት ተማከሩ፤


የኃያላኑን ሥጋ ትበላላችሁ፥ የምድር አለቆችን፥ የአውራ በጎችንና የጠቦቶችን፥ የፍየሎችንና የወይፈኖችን፥ የባሻንን ፍሪዳዎች ሁሉ ደም ትጠጣላችሁ።


ርስቴን የምትበዘብዙ እናንተ ሆይ! ደስ ቢላችሁ፥ ሐሤትንም ብታደርጉ፥ በማበራየት ላይም እንዳለች ጊደር ብትፈነጩ፥ እንደ ብርቱዎችም ፈረሶች ብታሽካኩ እንኳ፥


ጎሽ ከእነርሱ ጋር፥ ወይፈኖችም ከኮርማዎች ጋር ይወድቃሉ፤ ምድራቸውም በደም ትርሳለች፥ አፈራቸውም በስብ ትወፍራለች።


ነፍሴን እንደ አንበሳ ነጥቀው እንዳይሰብሩዋት፥ የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር።


አቤቱ፥ አንተ አየኸው፥ ዝም አትበል፥ አቤቱ፥ ከእኔ አትራቅ።


አቤቱ፥ አንተ አትጣለኝ፥ አምላኬ፥ ከኔ አትራቅ።


አቤቱ፥ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፥ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።


ከባርያህም ፊትህን አትሰውር፥ ተጨንቄአለሁና ፈጥነህ መልስልኝ።


አቤቱ፥ አድነኝ፥ አቤቱ፥ እኔን ለመርዳት ፍጠን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች