Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 21:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሕይወትን ለመነህ ሰጠኸውም፥ ለረጅም ዘመን ለዘለዓለም ዓለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በአቀዳጀኸው ድል ክብሩ ታላቅ ሆነ፤ ክብርንና ግርማን አጐናጸፍኸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አንተ በሰጠኸው ድሎች ምክንያት ታላቅ ክብር አገኘ፤ ክብርንና ግርማን አቀዳጀኸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ወደ አንተ ጮኹ፥ ዳኑም፥ አን​ተ​ንም አመኑ፥ አላ​ፈ​ሩም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 21:5
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ይህ በፊትህ ጥቂት ሆኖ ሳለ፤ አንተ ግን ስለ ወደ ፊቱ የአገልጋይህ ቤት ተናገርህ፤ ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ከሰው ጋር የምታደርገው ግንኙነት ለካ እንዲህ ነው?


አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በመንገዴ ብትሄድና ለእኔም ብትታዘዝ፥ ሕጌንና ትእዛዞቼንም ብትፈጽም ረጅም ዕድሜ እሰጥሃለሁ።”


ስለዚህ አሁን በፊትህ ለዘለዓለም እንዲኖር የባርያህን ቤት ለመባረክ ፈቅደሃል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ አንተ የባረከው ለዘለዓለም ይባረካል።”


የዳዊት መዝሙር። ጌታ ጌታዬን፦ “ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው።”


በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፥ በዚያ ጌታ በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘለዓለም አዝዞአልና።


ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦ አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።


ለንጉሥ ከቀን በላይ ቀን ትጨምራለህ፥ ዓመታቱም ከትውልድ ወደ ትውልድ ይሆናሉ።


እርሱ ዓለቴም መድኃኒቴም ነውና፥ እርሱ መጠጊያዬ ነው፥ አልታወክም።


ታስበው ዘንድ ሰው ምንድነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድነው?


ክብርና ግርማ በፊቱ፥ ኃይልና ውበት በመቅደሱ ውስጥ ናቸው።


ይህ ከኤዶምያስ፥ ልብሱም የቀላ ከባሶራ የሚመጣ፥ አለባበሱ ያማረ፥ በጉልበቱ ጽናት የሚራመድ ማን ነው? “በጽድቅ የምናገር ለማዳንም የምበረታ እኔ ነኝ።”


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።


ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ ዐይኖቹን አነሣና እንዲህ አለ፥ “አባት ሆይ! ሰዓቱ ደርሶአል፤ ልጅህ ያከብርህ ዘንድ ልጅህን አክብረው፤


እኛም አንድ እንደ ሆንን አንድ ይሆኑ ዘንድ የሰጠኸኝን ክብር ሰጥቻቸዋለሁ፤


አሁንም፥ አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር በፊት በአንተ ዘንድ በነበረኝ ክብር፥ በራስህ ዘንድ አንተ አክብረኝ።


እንግዲህ ከተናገርነው ነገር ዋናው ይህ ነው፦ በሰማያት በግርማው ዙፋን ቀኝ የተቀመጠ እንዲህ ያለ ሊቀ ካህናት አለን፤


እርሱም ወደ ሰማይ ሄዶ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ፤ መላእክትና ሥልጣናት ኀይላትም ተገዝተውለታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች