Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 20:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 እንደ ልብህ ምኞት ይስጥህ ፈቃድህንም ሁሉ ይፈጽምልህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በአንተ ድል ደስ ይበለን፤ በአምላካችን ስም አርማችንን ከፍ እናደርጋለን። እግዚአብሔር የለመንኸውን ሁሉ ይፈጽምልህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ድል በማድረግህ እልል እንላለን፤ በአምላካችንም ስም ዓርማችንን ከፍ እናደርጋለን፤ እግዚአብሔር ልመናህን ሁሉ ይፈጽምልህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በማ​ዳ​ንህ ክብሩ ታላቅ ነው፤ ክብ​ር​ንና ምስ​ጋ​ናን ጨመ​ር​ህ​ለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 20:5
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሙሴም መሠዊያ ሠራ፥ ስሙንም “ጌታ ሰንደቅ ዓላማዬ ነው” ብሎ ጠራው፤


ምድርን አናወጥሃት አወክሃትም፥ ተናውጣለችና ቁስልዋን ፈውስ።


ከዚያም ዔሊ፥ “በሰላም ሂጂ! የእስራኤል አምላክ የለመንሽውን ይስጥሽ!” አላት።


አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በጌታ እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።


በዚያም ቀን፦ እነሆ፥ አምላካችን ይህ ነው፤ ተስፋ አድርገነዋል፥ ያድነንማል፤ ጌታ ይህ ነው፤ ጠብቀነዋል፤ በማዳኑ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ይባላል።


መንፈሴም በአምላኬ በመድኃኒቴ ሐሴት ታደርጋለች፤


የእልልታና የመዳን ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይሉን አከናወነ።


ነፍሴ ግን በጌታ ደስ ይላታል፥ በማዳኑም ሐሴት ታደርጋለች።


ጠላቴ፦ “አሸነፍሁት እንዳይል”፥ የሚያስጨንቁኝም እኔ ብናወጥ ደስ እንዳይላቸው።


አቤቱ፥ እዘንልኝ፥ ጠላቶቼም የሚያመጡብኝን መከራ እይ፥ ከሞት ደጆች ከፍ ከፍ የምታደርገኝ፥


እኔ ግን በጌታ ደስ ይለኛል፤ በመድኃኒቴ አምላክ ሐሤት አደርጋለሁ።


ሕዝብ ሁሉ እያንዳንዱ በየአምላኩ ስም ይሄዳልና፥ እኛ ግን በጌታ አምላካችን ስም ለዘለዓለም ዓለም እንሄዳለን።


ንግግር የለም መናገርም የለም፥ ድምፃቸውም አይሰማም።


በዚያን ቀን፤ የእሴይ ሥር ለሕዝቦች ምልክት ሆኖ ይቆማል፤ መንግሥታት ወደ እርሱ ይመጣሉ፤ ማረፊያውም የከበረ ይሆናል።


ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።


ዳዊትም ፍልስጥኤማዊውን እንዲህ አለው፤ “አንተ ሰይፍ፥ ጦርና ጭሬ ይዘህ ትመጣብኛለህ፤ እኔ ግን አንተ በተገዳደርኸው የእስራኤል ሠራዊት አምላክ በሆነው፥ ሁሉን በሚችል በሠራዊት ጌታ ስም እመጣብሃለሁ።


የልቡን ፈቃድ ሰጠኽው፥ የከንፈሩንም ልመና አልከለከልኸውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች