Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 18:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ከአፍንጫው ጢስ ወጣ፥ ከአፉም የሚበላ እሳት ነደደ፥ ፍምም ከእርሱ በራ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 ሰማያትን ሰንጥቆ ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ሰማይን ሰንጥቆ ወደ ታች ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ንጹሕ ነው፥ ለዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ይኖ​ራል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፍርድ እው​ነ​ትና ቅን​ነት በአ​ን​ድ​ነት ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 18:9
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ይሹሩን ሆይ፥ በሰማያት ላይ ለረድኤትህ፥ በደመናትም ላይ በታላቅነት እንደሚሄድ እንደ ጌታ ያለ ማንም የለም።


ታላቅና ነጭ ዙፋን፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።


የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ በድንገት ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ ምድርም በእርሷም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።


ያንጊዜ ድምፁ ምድርን አናወጧት ነበር፤ አሁን ግን “አንድ ጊዜ ደግሜ እኔ ሰማይን አናውጣለሁ እንጂ ምድርን ብቻ አይደለም፤” ብሎ ተስፋ ሰጥቶአል።


ኢየሱስም መልሶ “እኔ የማደርገውን አንተ አሁን አታውቅም፤ በኋላ ግን ታስተውላለህ” አለው።


ከስድስት ሰዓት ጀምሮ እስከ ዘጠኝ ሰዓት ድረስ በምድር ሁሉ ላይ ጨለማ ሆነ።


“ከነዚያ ቀናት መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይሎችም ይናወጣሉ።


ጌታም በጽዮን ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይጮኻል፥ በኢየሩሳሌምም ሆኖ ቃሉን ያሰማል፥ ሰማይና ምድርም ይናወጣሉ፥ ጌታ ግን ለሕዝቡ መሸሸጊያ፥ ለእስራኤልም ልጆች መጠጊያ ይሆናል።


ሰማያትን ሰንጥቆ ወደ ታች ወረደ፤ ከእግሩም በታች ጥቅጥቅ ያለ ደመና ነበረ።


ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንሡ፥ ወደ ታችም ወደ ምድር ተመልከቱ፤ ሰማያትን እንደ ጢስ በንነው ይጠፋሉ፥ ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፥ የሚኖሩባትም እንዲሁ ይሞታሉ፤ ማዳኔ ግን ለዘለዓለም ይሆናል፥ ጽድቄም አይፈርስም።


ጻድቃንም ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ፥ በደስታም እልል ይበሉ።


ጌታ በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ ይጤስ ነበር፤ ጢሱም ከእቶን እንደሚወጣ ጢስ ይወጣ ነበር፥ ተራራውም ሁሉ እጅግ ተናወጠ።


አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፥ እሳት በፊቱ ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ ነፋስ አለ።


እሳት በፊቱ ይሄዳል፥ ጠላቶቹንም በዙሪያው ያቃጥላል።


እነሆ፥ ጌታ መዓቱን በቁጣ፥ ዘለፋውንም በእሳት ነበልባል ይመልስ ዘንድ ከእሳት ጋር ይመጣል፥ ሰረገሎቹም እንደ ዐውሎ ነፋስ ይሆናሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች