Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 149:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሃሌ ሉያ። ለጌታ አዲሱን ቅኔ ተቀኙለት፥ ውዳሴው በቅዱሳኑ ጉባኤ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሃሌ ሉያ። ለእግዚአብሔር አዲስ ቅኔ ተቀኙ፤ ምስጋናውንም በቅዱሳን ጉባኤ ዘምሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እግዚአብሔርን አመስግኑ! ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር ዘምሩ! በምእመናን ጉባኤ አመስግኑት!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አዲስ ምስ​ጋ​ናን አመ​ስ​ግ​ኑት፤ ምስ​ጋ​ና​ውም በጻ​ድ​ቃኑ ጉባኤ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 149:1
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አዲስ ቅኔም ተቀኙለት፥ በእልልታም መልካም ዝማሬ ዘምሩ፥


“መጽሐፉን ትወስድ ዘንድ ማኅተሞቹንም ትፈታ ዘንድ ይገባሃል ታርደሃልና፤ በደምህም ለእግዚአብሔር ከነገድ ሁሉ ከቋንቋም ሁሉ ከወገንም ሁሉ ከሕዝብም ሁሉ ሰዎችን ዋጅተህ፥ ለአምላካችን መንግሥትና ካህናት ይሆኑ ዘንድ አደረግሃቸው፤ በምድርም ላይ ይነግሣሉ፤” እያሉ አዲስን ቅኔ ይዘምራሉ።


እንዲህም በማለት፥ “ስምህን ለወንድሞቼ አበሥራለሁ፤ በማኅበርም መካከል በዜማ አመሰግንሃለሁ፤”


ሃሌ ሉያ። ጌታን ከሰማያት አመስግኑት፥ በአርያም አመስግኑት።


የዳዊት መዝሙር። ለጌታ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፥ ድንቅ ነገሮችን አድርጎአልና፥ ቀኙ፥ የተቀደሰ ክንዱም ለእርሱ ማዳን አደረገ።


ወደ ባሕር የምትወርዱ በእርሷም ውስጥ ያላችሁ ሁሉ፥ ደሴቶችና በእነርሱም ላይ የምትኖሩ፥ ለጌታ አዲስ መዝሙር፥ ከምድርም ዳርቻ ምስጋናውን ዘምሩ።


አቤቱ፥ አዲስ ቅኔ እቀኛልሃለሁ፥ ዐሥር አውታር ባለው በገና እዘምርልሃለሁ።


በሕዝቡ ሁሉ ፊት ስእለቴን ለጌታ እፈጽማለሁ፥


አለቆች ቀደሙ፥ መዘምራንም ተከተሉ፥ ከበሮን በሚመቱ በቈነጃጅት መካከል።


የችግረኛን ችግር አልናቀምና፥ ቸልም አላለምና፥ ፊቱንም አልሰወረምና፥ ነገር ግን ወደ እርሱ በጮኸ ጊዜ ሰማው።


ከአንበሳ አፍ አድነኝ፥ ከጐሽ ቀንድም ጠብቀኝ፥ መለስክልኝ!


ዘርህን ለዘለዓለም አዘጋጃለሁ፥ ዙፋንህንም ለልጅ ልጅ እመሠርታለሁ።


ለጌታ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፥ ምድር ሁሉ፥ ለጌታ ዘምሩ።


ሃሌ ሉያ! በቅኖች ሸንጎ በጉባኤም ጌታን በፍጹም ልቤ አመሰግንሃለሁ።


አቤቱ፥ በታላቁ ጉባኤ ውስጥ እገዛልሃለሁ፥ በብዙ ሕዝብ መካከልም አመሰግንሃለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች