Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 147:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታችን ታላቅ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር ስፍር የለውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ጌታችን ታላቅ ነው፤ እጅግ ኀያልም ነው፤ ለጥበቡም ወሰን የለውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አምላካችን ታላቅና ኀያል ነው፤ ለዕውቀቱም ወሰን የለውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 በረ​ዶ​ውን እንደ ባዘቶ ይሰ​ጣል፤ ጉሙን እንደ አመድ ይበ​ት​ነ​ዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 147:5
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ ታላቅ፥ ከፍ ያለ ምስጋናም ይገባዋልና፤ ከአማልክትም ሁሉ በላይ የተፈራ ነው።


እነሆ፥ እግዚአብሔር ኃያል ነው፥ ማንንም አይንቅም፥ እርሱም በጥበባዊ ኃይሉም ጽኑ ነው።


ጌታ ታላቅ እንደሆነ፥ ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንደሚበልጥ አውቄአለሁና።


ጌታ ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው፥ ታላቅነቱም የማይመረመር ነው።


ጌታን የታመነ ወደ ትዕቢተኛና ወደ ሐሰተኛ ያልተመለከተ ሰው ብፁዕ ነው።


በሁለተኛ ሰንበት የቆሬ ልጆች የምስጋና መዝሙር።


ጌታ ታላቅ፥ ምስጋናውም ብዙ ነውና፥ ከአማልክትም ሁሉ በላይ የተፈራ ነውና።


ጌታ በጽዮን ታላቅ ነው፥ እርሱም በአሕዛብ ሁሉ ላይ ከፍ ከፍ አለ።


አላወቅህም? አልሰማህም? ጌታ የዘለዓለም አምላክ ነው፤ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው፤ አይደክምም፤ አይታክትም፤ ማስተዋሉም አይመረመርም።


ጌታ ሆይ! እንደ አንተ ያለ የለም፤ አንተ ታላቅ ነህ ስምህም በኃይል ታላቅ ነው።


የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! በአሕዛብ ጥበበኞች ሁሉ መካከል በመንግሥታቸውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ ሌለ፥ አንተን መፍራት ይገባልና አንተን የማይፈራ ማን ነው?


ጌታ ለቁጣ የዘገየ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ በደለኛውንም፦ ንጹሕ ነህ አይልም፤ ጌታ መንገዱ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥ ነው፥ ደመናም የእግሩ ትቢያ ነው።


የእግዚአብሔር ባለጸግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው! ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው! መንገዱም የማይታወቅ ነው።


“ሁሉን የምትገዛ ጌታ አምላክ ሆይ! ሥራህ ታላቅና ድንቅ ነው፤ የአሕዛብ ንጉሥ ሆይ! መንገድህ ትክክልና እውነተኛ ነው፤ ጌታ ሆይ! የማይፈራህና ስምህን የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህና፤ የጽድቅም ሥራህ ስለ ተገለጠ አሕዛብ ሁሉ ይመጣሉ፤ በፊትህም ይሰግዳሉ፤” እያሉ የእግዚአብሔርን ባርያ የሙሴን ቅኔና የበጉን ቅኔ ይዘምራሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች