Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 146:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነ ተስፋውም በጌታ በአምላኩ የሆነ ሰው ምስጉን ነው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ብፁዕ ነው፤ ረዳቱ የያዕቆብ አምላክ የሆነ፣ ተስፋውንም በአምላኩ በእግዚአብሔር ላይ የጣለ ሰው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 የያዕቆብ አምላክ ረዳቱ የሆነለትና በአምላኩ በእግዚአብሔር ተስፋ ያደረገ ሰው ደስ ይበለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታላቅ ነው፥ ኀይ​ሉም ታላቅ ነው፥ ለጥ​በ​ቡም ቍጥር የለ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 146:5
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንደዚህ የሚሆንለት ሕዝብ የተመሰገነ ነው፥ ጌታ አምላኩ የሆነለት ሕዝብ ምስጉን ነው።


አቤቱ፥ አንተ ተስፋዬ ነህና፥ አቤቱ፥ ከታናሽነቴ ጀምረህ መታመኛዬ ነህና።


ጌታ አምላኩ የሚሆንለት ሕዝብ ምስጉን ነው፥ እርሱ ለርስቱ የመረጠው ሕዝብ።


ጌታ አምላክ ፀሐይና ጋሻ ነው፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፥ ጌታ በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያስቀራቸውም።


ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንሁ እወቁ፥ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።


እምነታችሁና ተስፋችሁ በእግዚአብሔር ይሆን ዘንድ፥ ከሞት ባስነሣው ክብርንም በሰጠው፥ በእግዚአብሔር በእርሱ ትተማመናላችሁ።


ከኃይል ወደ ኃይል ይሄዳሉ፥ የአማልክት አምላክ በጽዮን ይታያል።


አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተረበሹ፥ እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።


በእውነት ሰው እንደ ጥላ ይመላለሳል፥ በእውነት በከንቱ ይታወካል። ያከማቻል የሚሰበስብለትንም አያውቅም።


እርሱም፦ “እኔ የአባትህ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅ አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” አለው። ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ማየት ፈርቶ ፊቱን ሸፈነ።


እስራኤል ሆይ፥ ምስጉን ነህ፥ በጌታ የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን ነው? እርሱ የረድኤትህ ጋሻ፥ የከፍተኛነትህም ሰይፍ ነው። ጠላቶችህም ይገዙልሃል፥ አንተም ከፍታቸውን ትረግጣለህ።”


ዮሴፍን እንዲህ በሉት፦ ‘እባክህ የወንድሞችህን በደል ኃጢአታቸውንም ይቅር በል፥ እነርሱ በአንተ ከፍተውብሃልና፥ አሁንም እባክህ የአባትህ አምላክ ባርያዎች የበደሉህን ይቅር በል።’”


እነኚህ በሠረገላ እነዚያም በፈረስ ይታመናሉ፥ እኛ ግን በአምላካችን በጌታ ስም ከፍ ከፍ እንላለን።


የሠራዊት ጌታ ከእኛ ጋር ነው፥ የያዕቆብ አምላክ መጠጊያችን ነው።


ቃልን የሚያዳምጥ መልካም ነገርን ያገኛል፥ በጌታ የታመነ ምስጉን ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች