17 ጌታ በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ ነው በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።
17 እግዚአብሔር በመንገዱ ሁሉ ጻድቅ፣ በሥራውም ሁሉ ቸር ነው።
17 እግዚአብሔር በሚያደርገው ሁሉ እውነተኛ ነው፤ በሥራውም ሁሉ ታማኝ ነው።
ይህ ከአንተ ይራቅ፥ ጻድቁን ከኃጢአተኛ ጋር ትገድል ዘንድ፥ ጻድቁም እንደ ኃጢአተኛ ይሆን ዘንድ፥ እንደዚህ ያለው አድራጎት ከአንተ ይራቅ። የምድር ሁሉ ፈራጅ በቅን ፍርድ አይፈርድምን?”
የአምላክ መንገዱ ፍጹም ነው፤ የጌታም ቃል የጠራ ነው፤ ለሚታመኑበትም ሁሉ ጋሻ ነው፤
“ስለዚህ የምታስተውሉ ሰዎች፥ ስሙኝ፥ ክፋትን ማድረግ ከእግዚአብሔር፥ በደልንም መፈጸም ሁሉን ከሚችል አምላክ ይራቅ።
በእውነት እግዚአብሔር ክፉ አይሠራም፥ ሁሉንም የሚችል አምላክ ፍርድን ጠማማ አያደርግም።
ጌታ ጽድቅን ይፈጽማል፥ ለተበደሉ ሁሉ ይፈርዳል።
ለቅኖች ብርሃን በጨለማ ወጣ፥ መሓሪ፥ ርኅሩኅና ጻድቅ ነው።
ጌታ መሓሪና ጻድቅ ነው፥ አምላካችንም ርኅሩኅ ነው።
ሰማያት ጽድቁን ይናገራሉ፥ እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና።
ኃያል ክንድ አለህ፥ እጅህ በረታች ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች።
ደመና ጭጋግም በዙሪያው ናቸው፥ ጽድቅና ፍርድ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።
ይናገሩ ይቅረቡም በአንድነትም ይማከሩ፤ ከጥንቱ ይህን ያሳየ ከቀድሞስ የተናገረ ማን ነው? ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ ጌታ አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኃኒት ነኝ፥ ከእኔም በቀር ማንም የለም።
በውስጧ ያለው ጌታ ጻድቅ ነው፥ ስሕተት አያደርግም፥ ማለዳ ማለዳ ፍርዱን ለብርሃን ይሰጣል፥ አያቋርጥምም፤ ዓመፀኛው ግን እፍረትን አያውቅም።
አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ! አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ! እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።
“እርሱ ዐለት፥ ሥራውም ፍጹም ነው፤ መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፥ የታመነ አምላክ፥ ተንኮል የሌለበት፥ እርሱ ቀጥተኛና ጻድቅ ነው።
ሰማይም ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆም ነጭ ፈረስ፤ የተቀመጠበትም የታመነና እውነተኛ ይባላል፤ በጽድቅም ይፈርዳል፤ ይዋጋልም።
ፍርዶቹ እውነትና ጽድቅ ናቸውና፤ በዝሙትዋ ምድርን ያበላሸችውን ታላቂቱን አመንዝራ ፈርዶባት፥ የባርያዎቹንም ደም ከእጅዋ ተበቀሎአልና።
አራቱም ሕያዋን ፍጡራን እያንዳንዳቸው ስድስት ክንፎች አሉአቸው፤ በዙሪያቸውና በውስጣቸውም ዐይኖች ሞልተውባቸዋል፤ “ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የነበረውና ያለ የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ” ከማለት ቀንና ሌሊት አያርፉም ነበር።