Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 139:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አቤቱ፥ የሚጠሉህን እኔ የጠላሁ አይደለሁምን? በአንተ ላይ የሚነሡትንም አልናቅሁምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚጠሉህን አልጠላምን? በአንተ ላይ የሚነሡትንስ አልጸየፍምን?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እግዚአብሔር ሆይ! የሚጠሉህን እጅግ እጠላቸዋለሁ! በአንተ ላይ የሚያምፁትንም እጅግ እጸየፋቸዋለሁ!

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 139:21
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቃልህን አልጠበቁምና ሰነፎችን አይቼ አዘንሁ።


በእጅህ ነፍሴን አደራ እሰጣለሁ፥ የእውነት አምላክ አቤቱ፥ ተቤዥተኸኛል።


“ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንደማትችል፥ እንዲሁም ሐዋርያት ሳይሆኑ ‘ነን’ የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤


ባለ ራእዩ የአናኒ ልጅ ኢዩ ሊገናኘው ወጣ፥ ንጉሡንም ኢዮሣፍጥን እንዲህ አለው፦ “ከሐዲውን ታግዛለህን? ወይስ ጌታን የሚጠሉትን ትወድዳለህን? ስለዚህም ነገር ከጌታ ዘንድ ቁጣ ሆኖብሃል።


ነገር ግን ይህ አለህ፤ እኔም የምጠላውን የኒቆላውያንን ሥራ ትጠላለህ።


የክፉ አድራጊዎቸን ማኅበር ጠላሁ፥ ከክፉዎችም ጋር አልቀመጥም።


ሲቀርብም ከተማይቱን አይቶ እንዲህ እያለ አለቀሰላት፤


ስለ ልባቸውም ድንዛዜ አዝኖ፥ ዙሪያውን በቁጣ ተመለከተና ሰውየውን፦ “እጅህን ዘርጋ፤” አለው። እርሱም ዘረጋ፤ እጁም ዳነች።


ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የጌታም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ እጅግ ታነባለች፥ እንባንም ታፈስሳለች።


ሕግህን አልጠበቅሁምና የውኃ ፈሳሽ ከዐይኖቼ ፈሰሰ።


ኃጢአተኛ ሰው በፊቱ የተናቀ፥ ጌታን የሚፈሩትን የሚያከብር፥ ቢጎዳም የማለውን የማይከዳ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች