26 የሰማይን አምላክ አመስግኑ፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።
26 የሰማይን አምላክ አመስግኑ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
26 ይህን ሁሉ ስላደረገ ለሰማይ አምላክ ምስጋና አቅርቡ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
እርሱም፦ “እኔ ዕብራዊ ነኝ፥ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን፥ የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ” አላቸው።
እነዚህን ቃላት በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ። ለብዙ ቀኖች አዘንሁ፤ በሰማይ አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥
የዕርገት መዝሙር። በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዐይኖቼን ወደ አንተ አነሣሁ።
አምላካችንስ በላይ በሰማይ ነው፥ የፈቀደውን ሁሉ አደረገ።
በዚያም ሰዓት ታላቅ የምድር መናወጥ ሆነ፤ ከከተማይቱም ዐሥረኛው እጅ ወደቀ፤ በመናወጥም ሰባት ሺህ ሰዎች ተገደሉ፤ የቀሩትንም ፍርሃት ያዛቸው፤ ለሰማዩም አምላክ ክብር ሰጡ።
ንጉሡም፦ “ምን ትፈልጋልህ?” አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አምላክ ጸለይሁ።