23 እኛን በመዋረዳችን አስቦናልና፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
23 በውርደታችን ጊዜ ያሰበን፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
23 በተሸነፍን ጊዜ አልረሳንም፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
በጭንቃቸው ሁሉ እርሱ ተጨነቀ፥ የፊቱም መልአክ አዳናቸው፤ በፍቅሩና በርኅራኄውም ተቤዣቸው፥ በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንሥቶ ተሸከማቸው።
እኔን ዝቅተኛይቱን አገልጋይ ተመልክቶአልና። እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል፤
አቤቱ፥ ወደ አንተ ጮኽሁ፦ አንተ መጠጊያዬ ነህ፥ በሕያዋንም ምድር አንተ እድል ፈንታዬ ነህ አልሁ።
ጌታ የዋሆችን ይጠብቃል፥ ተዋረድሁ፥ እርሱም አዳነኝ።
ከመኰንኖች ጋር ከሕዝቡም መኰንኖች ጋር ያኖረው ዘንድ ችግረኛን ከመሬት የሚያነሣ፥ ምስኪኑንም ከፋንድያ ከፍ ከፍ የሚያደርግ፥
ጌታ ለሕዝቡ ይፈርዳል፥ ለአገልጋዮቹም ያዝናል። ኃይላቸውም እንደደከመ፥ የታሰረም ሆነ የተለቀቀ እንደሌለ ሲያዩ፥
ገዥዎችን ከዙፋናቸው አውርዶአል፤ ትሑታንንም ከፍ አድርጎአል፤
ጌታ ጽዮንን ይሠራታልና፥ በክብሩም ይገለጣልና።
እግዚአብሔር ኖኅንና ከእርሱ ጋር በመርከቡ ውስጥ የነበሩትን አራዊትና እንስሶች ሁሉ አሰበ። ነፋስ በምድር ላይ እንዲነፍስ አደረገ፥ ውኃውም ጎደለ፥