13 የኤርትራን ባሕር በየክፍሉ የከፈለውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥
13 ቀይ ባሕር ለሁለት የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና።
13 ቀይ ባሕርን ከፈለ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው።
ባሕርን ከፍሎ አሳለፋቸው፥ ውኆችን እንደ ግንብ አቆመ።
በደረቅ ምድር እንደሚያልፉ የኤርትራን ባሕር በእምነት ተሻገሩ፤ የግብጽ ሰዎች ግን ሲሞክሩ ሰመጡ።
አንተ ባሕርን በኃይልህ ከፈልካት፥ የአውሬዎችን ራስ በውኃ ውስጥ ሰበርህ።
የእስራኤል ልጆች ግን በባሕሩ ውስጥ በደረቅ ምድር ተራመዱ፤ ውኆችም በቀኛቸውና በግራቸው ግድግዳ ሆኑላችው።