Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 132:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ጌታ ጽዮንን መርጦአታልና፥ ማደሪያውም ትሆነው ዘንድ ወድዶአታልና፥ እንዲህ ብሎ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እግዚአብሔር ጽዮንን መርጧታልና፣ ማደሪያውም ትሆን ዘንድ ወድዷልና እንዲህ አለ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር ጽዮንን መርጦአታል፤ መኖሪያውም ሊያደርጋት ይፈልጋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 132:13
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከልጅህም ቢሆን መንግሥቱን በሙሉ አልወስድበትም፤ ለአገልጋዬ ለዳዊትና ለራሴ ርስት እንድትሆን ለመረጥኳት ለኢየሩሳሌም ከተማ ስል አንድ ነገድ እተውለታለሁ።”


አሁንም ስሜ ለዘለዓለም በዚያ እንዲኖር ይህን ቤት መርጫለሁ ቀድሻለሁም፤ ዐይኖቼና ልቤም ዘወትር በዚያ ይሆናሉ።


ከሕዝቡ ሁሉ ማንም በእናንተ ውስጥ የሚኖር አምላኩ ከእርሱ ጋር ይሁን፥ እርሱም በይሁዳ ወዳለችው ወደ ኢየሩሳሌም ይውጣ፥ የጌታ የእስራኤል አምላክን ቤት ይሥራ፥ እርሱም በኢየሩሳሌም ያለ አምላክ ነው፤


መለኮታዊ ተራራ፥ የባሳን ተራራ፥ የጸና ተራራና የባሳን ተራራ።


ከያዕቆብ ድንኳኖች ይልቅ፥ ጌታ የጽዮንን ደጆች ይወድዳቸዋል።


በጽዮን ለሚኖር ለጌታ ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል ድንቅ ሥራውን ንገሩ፥


ለሕዝቡም መልእክተኞች ምን ብሎ መልስ ይሰጣል? “ጌታ ጽዮንን መሥርቷል፥ ከሕዝቡም ችግረኞች በእርሷ ውስጥ መጠጊያን ያገኛሉ።”


ነገር ግን ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕያው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል፤ ወደ ሰማያዊቱም ኢየሩሳሌም፥ በደስታም ወደ ተሰበሰቡት ወደ አእላፋት መላእክት፥


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች