Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 13:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 አቤቱ፥ እስከ መቼ ፈጽመህ ትረሳኛለህ? እስከ መቼስ ፊትህን ከእኔ ትሰውራለህ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከሐሳቤ ጋራ የምሟገተው፣ ልቤም ቀኑን ሙሉ የሚያዝነው እስከ መቼ ነው? ጠላቴስ በእኔ ላይ የሚያይለው እስከ መቼ ድረስ ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ችግርን እስከ መቼ መቻል ይኖርብኛል? እስከ መቼ ልቤ ቀንና ሌሊት በሐዘን ይሞላል? እስከ መቼስ ጠላቴ በእኔ ላይ የበላይነትን ያገኛል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 የሚ​ያ​ስ​ተ​ውል፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የሚ​ፈ​ልግ እን​ዳለ ያይ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ማይ የሰው ልጆ​ችን ተመ​ለ​ከተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 13:2
44 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሡም፦ “አልታመምክም ታዲያ ፊትህ ለምን አዘነ? ይህ የልብ ኃዘን ነው እንጂ ሌላ ነገር አይደለም” አለኝ። እኔም እጅግ በጣም ፈራሁ።


በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፥ ጻድቅም ብሆን ራሴን አላነሣም፥ ጉስቁልናን ተሞልቻለሁና፥ መከራዬንም ተመልክቻለሁና።


ፍርዱ ለወላጅ አልባና ለተጨቆነ ይደረግ ዘንድ፥ ሰዎች በምድር ላይ ማሸበራቸውን እንዳይቀጥሉ።


የሞት ገመዶች ወጠሩኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፥ ጭንቀትንና መከራን አገኘሁ።


ከሚያስጨንቁኝ ከኃጢአተኞች፥ ነፍሴንም ከሚከብቡአት ከጠላቶቼ።


አቤቱ፥ አንተን ጠርቻለሁና አልፈር፥ ክፉዎች ይፈሩ በሲኦልም ዝም ይበሉ።


ጠላቶቼ በእኔ ላይ ደስ እንዳይላቸው ብያለሁና፥ እግሮቼም ቢሰናከሉ ራሳቸውን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።


ዘወትር፦ አምላክህ ወዴት ነው? ሲሉኝ እንባዬ በቀንና በሌሊት ምግብ ሆነኝ።


ነፍሴም እጅግ ታወከች፥ አንተም አቤቱ፥ እስከ መቼ ድረስ ነው?


አቤቱ አምላኬ፥ በአንተ ታመንሁ፥ ከሚያሳድዱኝ ሁሉ አድነኝና አውጣኝ፥


አቤቱ፥ ጠላት እስከ መቼ ይሳደባል? ስምህን ጠላት ለሁልጊዜ ያቃልላልን?


ይህንንም አስታውስ፥ ጠላት በጌታ ተሳለቀ፥ አላዋቂ ሕዝብም በስምህ ቀለደ።


አቤቱ ጌታችን፥ ስምህ በምድር ሁሉ ምን ያህል ገናና ነው፥ ክብርህን በሰማዮች ላይ የምታኖር።


አሕዛብን ገሠጽህ፥ ክፉዎችንም አጠፋህ፥ ስማቸውንም ለዘለዓለም ደመሰስህ።


ደስ ያለው ልብ ፊትን ያበራል፥ በልብ ኀዘን ግን ነፍስ ትሰበራለች።


እነሆ፥ እኔ ያየሁት መልካምና የተዋበ ነገር ቢኖር ሰው እግዚአብሔር በሰጠው በሕይወቱ ዘመን ሁሉ ሲበላና ሲጠጣ፥ ከፀሐይ በታችም በሚደክምበት ድካም ሁሉ ደስ ሲለው ነው፥ ይህ እድል ፈንታው ነውና።


ለምን ሕመሜ የማያቋርጥ ሆነ? ቁስሌስ የማይፈወስ ለምን ሆነ? ለምንስ፦ አልሽርም አለ? በውኑ እንደ ሐሰተኛ ምንጭ፥ እንዳልታመነች ውኃ ትሆንብኛለህን?


አንተ፦ ‘ጌታ በሕመሜ ላይ ኀዘንን ጨምሮብኛልና ወዮልኝ! በልቅሶዬ ጩኸት ደክሜአለሁ፥ ዕረፍትንም አላገኘሁም’ ብለሃል።


ኀዘኔ የማይጽናና ነው፥ ልቤም በውስጤ ደክሞአል።


ሄ። ስለ ኃጢአትዋ ብዛት እግዚአብሔር አስጨንቆአታልና አስጨናቂዎችዋ ራስ ሆኑ ጠላቶችዋም ተከናወነላቸው፥ ሕፃናቶችዋ በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል።


ጤት። አደፍዋ በልብስዋ ዘርፍ ነበረ፥ ፍጻሜዋን አላሰበችም፥ ስለዚህ በድንቅ ተዋርዳለች፥ የሚያጽናናትም የለም፥ አቤቱ፥ ጠላት ከፍ ከፍ ብሏልና መከራዬን ተመልከት።


ስለምን ለዘለዓለም ትረሳናለህ? ስለ ምንስ ለረጅም ዘመን ትተወናለህ?


“ነፍሴ እስከ ሞት ድረስ እጅግ አዝናለች፤ እዚህ ቆዩ፤ ከእኔም ጋር ትጉ” አላቸው።


ዕለት ዕለት ከእናንተ ጋር በመቅደስ ስሆን እጆቻችሁን አልዘረጋችሁብኝም፤ ሆኖም ይህ የእናንተ ጊዜና ጨለማው የሚሰፍንበት ወቅት ነው፤” አላቸው።


ነገር ግን ይህን ስለ ነገርኋችሁ ኀዘን በልባችሁ ሞልቶአል።


ታላቅ ኃዘን የማያቋርጥም ሥቃይ በልቤ አለ።


በእርግጥ በጠና ታሞ ለሞት ተቃርቦ ነበርና፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ማረው፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ያደረገው ለእርሱ ብቻ ሳይሆን ኀዘን በኀዘን ላይ እንዳይደራረብብኝ ለእኔም ደግሞ ነው።


ሳኦል ከቀድሞው ይልቅ ዳዊትን ፈራው፤ እስከ ዕድሜ ልኩም ጠላቱ ሆነ።


ያደረግህልኝን በጎ ነገር ይኸው ነግረኸኛል፤ ጌታ እኔን በእጅህ ቢጥልልህም አንተ ግን አልገደልኸኝም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች