95 ኃጢአተኞች ያጠፉኝ ዘንድ ጠበቁኝ፥ ምስክርህን ግን መረመርሁ።
95 ክፉዎች ሊያጠፉኝ አድብተዋል፤ እኔ ግን ምስክርነትህን አሰላስላለሁ።
95 ክፉዎች እኔን ለመግደል ያደባሉ፤ እኔ ግን ሕግህን አሰላስላለሁ።
ነፍሴ ምስክርህን ጠበቀች እጅግም ወደደችው።
አቤቱ፥ ሕግህን ተጠጋሁ፥ አታሳፍረኝ።
የትዕቢተኞች ዓመጽ በላዬ በዛ፥ እኔ ግን በፍጹም ልቤ ትእዛዛትህን እፈልጋለሁ።
ጳውሎስንም ሲቃወም እንዲያደላላቸው እየለመኑ፥ በመንገድ ሸምቀው ይገድሉት ዘንድ አስበው ወደ ኢየሩሳሌም እንዲያስመጣው ማለዱት።
እንግዲህ አንተ በጅ አትበላቸው፤ እስኪገድሉት ድረስ እንዳይበሉና እንዳይጠጡ ተማምለው ከእነርሱ ከአርባ የሚበዙ ሰዎች ያደቡበታልና፤ አሁንም የተዘጋጁ ናቸው፤ የአንተንም ምላሽ ይጠብቃሉ፤” አለው።
ጴጥሮስም ወደ ልቡ ተመልሶ “ጌታ መልአኩን ልኮ ከሄሮድስ እጅና የአይሁድ ሕዝብ ይጠብቁት ከነበረው ሁሉ እንደ አዳነኝ አሁን በእውነት አወቅሁ፤” አለ።
ምስክሮችህ ድንቆች ናቸው፥ ስለዚህ ነፍሴ ፈለገቻቸው።
እኔ ባርያህ ነኝ፥ እንዳስተውል አድርገኝ፥ ምስክርህንም አውቃለሁ።
የኀጥኣን ገመዶች ተተበተቡብኝ፥ ሕግህን ግን አልረሳሁም።
ሕግህም ተድላዬ ነው፥ ደንቦችህም አማካሪዎቼ ናቸው።
ወዳጆቼም ባልንጀሮቼም ከቁስሌ ገለል ብለው ቆሙ፥ ዘመዶቼም ርቀው ቆሙ።
ክፉ ጻድቁን ይመለከተዋል፥ ሊገድለውም ይወድዳል።
ክፉዎች፥ አስጨናቂዎቼ ጠላቶቼም፥ ሥጋዬን ለመብላት በቀረቡ ጊዜ፥ እነርሱ ተሰናከሉና ወደቁ።
የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘለዓለም ወረስሁ።