47 እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል።
47 እኔ እወድደዋለሁና፣ በትእዛዝህ ደስ ይለኛል።
47 በትእዛዞችህ የምደሰተው እነርሱን ስለምወዳቸው ነው።
እጆቼንም ወደ ወደድኋቸው ወደ ትእዛዛትህ አነሣለሁ፥ ሥርዓትህንም አሰላስላለሁ።
አቤቱ፥ ሕግህን እንደምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው።
ስለዚህ ከወርቅና ከዕንቁ ይልቅ ትእዛዝህን ወደድሁ።
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ ማድረግ፥ ሥራውንም መፈጸም ነው።
በድንጋጌዎችህ ደስ ይለኛል፥ ቃልህንም አልረሳም።
በውስጣዊ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና፥
አቤቱ፥ ማዳንህን ናፈቅሁ፥ ሕግህም ተድላዬ ነው።
ነፍሴ ምስክርህን ጠበቀች እጅግም ወደደችው።
ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው፥ ባርያህም ወደደው።
ሃሌ ሉያ። ጌታን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ብፁዕ ነው።
ለዚህ ተጠርታችኋል፤ ምክንያቱም ክርስቶስ ስለ እናንተ መከራን የተቀበለው የእርሱን አርአያነት እንድትከተሉ ምሳሌን ሊተውላችሁ ነው።
ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው፤ ትእዛዙም ቅዱስ፥ ትክክለኛና መልካም ነው።
ሕግህም ተድላዬ ነው፥ ደንቦችህም አማካሪዎቼ ናቸው።
በክርስቶስ ኢየሱስ የነበረ ይህ አሳብ በእናንተ ዘንድ ደግሞ ይኑር።
እንግዲህ የማልፈልገውን ነገር የማደርግ ከሆነ ሕግ ትክክል ነው እላለሁ።
ዓመፀኞችን ጠላሁ፥ ሕግን ግን ወደድሁ።
የምድርን ኃጢአተኞች ሁሉ እንደ ርኩሰት አጠፋሃቸው፥ ስለዚህ ምስክርህን ወደድሁ።
ትእዛዝህን እንደ ወደድሁ ተመልከት፥ አቤቱ፥ በምሕረትህ ሕያው አድርገኝ።
ዓመፃን ጠላሁ ተጸየፍሁም፥ ሕግህን ግን ወደድሁ።