174 አቤቱ፥ ማዳንህን ናፈቅሁ፥ ሕግህም ተድላዬ ነው።
174 እግዚአብሔር ሆይ፤ ማዳንህን ናፈቅሁ፤ ሕግህም ደስታዬ ነው።
174 እግዚአብሔር ሆይ! አዳኝነትህን እናፍቃለሁ፤ በሕግህም ደስ ይለኛል።
በድንጋጌዎችህ ደስ ይለኛል፥ ቃልህንም አልረሳም።
ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።
የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘለዓለም ወረስሁ።
እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል።
ነገር ግን በጌታ ሕግ ደስ የሚለው፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት የሚያስብ።
በእነዚህም በሁለቱ አማራጮች መካከል እጨነቃለሁ፤ ልሄድ ከክርስቶስም ጋር ልኖር እናፍቃለሁ፤ ከሁሉ ይልቅ እጅግ የሚሻል ነውና፤
የምትዘገይ ተስፋ ልብን ታሳዝናለች፥ የተገኘች ፈቃድ ግን የሕይወት ዛፍ ናት።
ነፍሴ መድኃኒትህን ናፈቀች፥ በቃልህም ታመንሁ።
ሕግህ ተድላዬ ናትና ቸርነትህ ትምጣልኝ፥ በሕይወትም ልኑር።
ሕግህም ተድላዬ ነው፥ ደንቦችህም አማካሪዎቼ ናቸው።
ሁሉንም ነገር አዘጋጅቶና ጠብቆ፥ ከእኔ ጋር ዘላለማዊ ኪዳን ያደረገ፥ መዳኔን ከፍጻሜ የሚያደርሰው፥ መሻቴን ሁሉ የሚሰጠኝ እርሱ አይደለምን? በውኑ ቤቴ በእግዚአብሔር ዘንድ እንዲህ አይደለምን?
ጌታ ሆይ፥ መድኃኒትህን እጠብቃለሁ።
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ አስምላችኋለሁ፥ ውዴን ያገኛችሁት እንደሆነ፥ እኔ ከፍቅር የተነሣ መታመሜን ንገሩት።
አቤቱ፥ እንደ ቃልህ፥ ምሕረትህና መድኃኒትህ ይምጡልኝ።