162 ብዙ ምርኮ እንዳገኘ በቃልህ ደስ አለኝ።
162 ትልቅ ምርኮ እንዳገኘ ሰው፣ በቃልህ ደስ አለኝ።
162 ብዙ ምርኮ አግኝቶ እንደሚደሰት ሰው በተስፋ ቃልህ እጅግ ደስ ይለኛል።
ቃላትህ ተገኝተዋል እኔም በልቼአቸዋለሁ፤ አቤቱ! የሠራዊት አምላክ ጌታ ሆይ! በስምህ ተጠርቻለሁና ቃላትህ ሐሤትና የልብ ደስታ ሆኑኝ።
ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የአፍህ ሕግ ይሻለኛል። ዮድ።
የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘለዓለም ወረስሁ።
ዳዊትን ወደ ታች መርቶ ባደረሰው ጊዜም፥ እነሆ ወራሪዎቹ ከፍልስጥኤማውያንና ከይሁዳ ምድር ከወሰዱት ታላቅ ምርኮ የተነሣ በየቦታው ተበታትነው ይበሉ፥ ይጠጡና ይዘፍኑ፥ ይጨፍሩም ነበር።
ምድያም ድል በተመታ ጊዜ እንደ ሆነው፤ የከበዳቸውን ቀንበር፤ በትከሻቸው ላይ የነበረውን በትር፤ የተጨቈኑበትንም ዘንግ ሰብረህላቸዋል።
ከዕቡያን ጋር ምርኮ ከመካፈል ከትሑታን ጋር በተዋረደ መንፈስ መሆን ይሻላል።
በብልጽግና እንደሚደሰቱ ሁሉ በሕጎችህ መንገድ ደስ አለኝ።