Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 119:155 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

155 መድኃኒት ከኀጥኣን ሩቅ ነው፥ ሥርዓትህን አልፈለጉምና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

155 ሥርዐትህን ስለማይሹ፣ ድነት ከክፉዎች የራቀ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

155 ሕግህን ስለማይፈልጉ ክፉዎች የመዳን ተስፋ የላቸውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 119:155
11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልጆቹም ከደኅንነት ርቀዋል፥ በበርም ውስጥ ተረግጠዋል፥ የሚደርስላቸውም የለም።


የሚያስተውል የለም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልግ የለም፤


እርሱም እየጮኸ ‘አብርሃም አባት ሆይ! ማረኝ፤ በዚህ ነበልባል እሠቃያለሁና የጣቱን ጫፍ በውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ላክልኝ፤’ አለ።


የከንፈሮችን ፍሬ እፈጥራለሁ፤ በሩቅም በቅርብም ላለው ሰላም ሰላም ይሁን፥ እፈውሰውማለሁ፥ ይላል ጌታ።


እናንተ ከጽድቅ የራቃችሁ እልከኞች፥ ስሙኝ፤


የዕውቀት መጀመሪያ ጌታን መፍራት ነው፥ ሞኞች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።


ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፥ ከጠማማም ጋር ብልህ ሆነህ ትገኛለህ።


ክፉ በትዕቢቱ ጌታን አይፈልገውም፥ በሐሳቡ በሙሉ እግዚአብሔር የለም።


ሁላችን እንደ ድቦች እንጮኻለን፤ እንደ ርግብ በመቃተት እንጮኻለን፤ ፍትህን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር እርሱ ግን የለም፤ መዳንም ከእኛ ዘንድ ርቆአል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች