140 ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው፥ ባርያህም ወደደው።
140 ቃልህ እጅግ የነጠረ ነው፤ ባሪያህም ወደደው።
140 የተስፋ ቃልህ እጅግ የታመነ ነው፤ እኔም በጣም እወደዋለሁ።
የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ የጠራ ነው፥ እርሱ ለሚታመኑት ጋሻ ነው።
የጌታ ሕግ ፍጹም ነው፥ ነፍስን ይመልሳል፥ የጌታ ምስክር የታመነ ነው፥ የዋሆችን ጠቢባን ያደርጋል።
ስለ ምስኪኖች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት ጌታ፦ አሁን እነሣለሁ ይላል፥ የተጠሙትንም ደኅንነት አመጣላቸዋለሁ።
ማንኛውም ትንቢት በሰው ፈቃድ ከቶ አልመጣም፤ ነገር ግን ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ የተመሩ ሰዎች ከእግዚአብሔር ተቀብለው ተናገሩ።
በውስጣዊ ሰውነቴ በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለኛልና፥
ስለዚህ ሕጉ ቅዱስ ነው፤ ትእዛዙም ቅዱስ፥ ትክክለኛና መልካም ነው።
ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ፥ አዲስ እንደ ተወለዱ ሕፃናት ንጹሑን መንፈሳዊ ወተት ተመኙ፤
ስለዚህ ወደ ትእዛዝህ ሁሉ አቀናሁ፥ የዓመፅንም መንገድ ሁሉ ጠላሁ።
በአንተ ግብረ ኃይል አጠቃለሁ፥ በአምላኬም ቅጥሩን እዘልላለሁ።
እንግዲህ የማልፈልገውን ነገር የማደርግ ከሆነ ሕግ ትክክል ነው እላለሁ።
በምድር ምድጃ ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር የጌታ ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።
እጅግም በወደድኋቸው በትእዛዛትህ ደስ ይለኛል።