Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 118:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ጌታ አምላክ ነው፥ ለእኛም አበራልን፥ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ፥ ቅርንጫፎች ይዘን፥ ለበዓሉ ዑደት እናድርግ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ብርሃኑንም በላያችን አበራ፤ እስከ መሠዊያው ቀንዶች ድረስ በመውጣት፣ ዝንጣፊ ይዛችሁ በዓሉን ከሚያከብሩት ጋራ ተቀላቀሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 እግዚአብሔር አምላክ ነው፤ ብርሃንን ሰጥቶናል፤ ለምለም የሆኑ ቅርንጫፎችን ይዘን በዓል ለማክበር ወደ መሠዊያው እንሂድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 የእ​ው​ነ​ት​ህን መን​ገድ እን​ዳ​ስ​ተ​ውል አድ​ር​ገኝ፥ ተአ​ም​ራ​ት​ህ​ንም አሰ​ላ​ስ​ላ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 118:27
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ ጌታ እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።


ሰዎቹም ይህን ባዩ ጊዜ በግንባራቸው መሬት ላይ ተደፍተው በመደነቅ “ጌታ አምላክ ነው! እውነተኛ አምላክ እርሱ ብቻ ነው!” አሉ።


በማግስቱም ለጌታ መሥዋዕት ሰዉ፥ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ለጌታ አቀረቡ፤ አንድ ሺህ ወይፈን፥ አንድ ሺህም አውራ በጎች፥ አንድ ሺህም የበግ ጠቦቶች፥ የመጠጥ ቁርባናቸውንም፥ ስለ እስራኤልም ሁሉ ብዙ መሥዋዕት አቀረቡ።


አንተ የተጠቃውን ሕዝብ ታድናለህና፥ የትዕቢተኞችን ዐይን ግን ታዋርዳለህ።


ጽድቅህን እንደ ብርሃን። ፍርድህንም እንደ ቀትር ያመጣዋል።


በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን አድርግለት፥ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ይሁኑ፤ በነሐስም ለብጠው።


በአራቱም ማዕዘን ቀንዶችን አደረገበት፤ ቀንዶቹም ከእርሱ ጋር ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ፤ በነሐስም ለበጠው።


ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የጌታም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ።


ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፤ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፤ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።


በእርሱ ላይ ኃጢአት ሠርቻለሁና፥ ጉዳዬን እስኪምዋገትልኝ ድረስ፥ ፍርድን እስኪያደርግልኝ ድረስ የጌታን ቁጣ እታገሣለሁ። ወደ ብርሃን ያወጣኛል፥ ጽድቁንም አያለሁ።


ስሜን ለምትፈሩት ለእናንተ ግን የጽድቅ ፀሐይ ትወጣላችኋለች፥ ፈውስም በክንፎችዋ ውስጥ ይሆናል፤ እናንተም ትወጣላችሁ፥ ከጋጣ እንደ ወጡ ጥጃዎች ትቦርቃላችሁ።


ደግሞም ኢየሱስ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይሆንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም” ብሎ ተናገራቸው።


እንግዲህ ዘወትር ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት አድርገን በእርሱ በኩል እናቅርብለት።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን አስደናቂ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ እግዚአብሔር ለራሱ ያደረጋችሁ ቅዱስ ሕዝብ ናችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች