Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 118:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 የእልልታና የመዳን ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው፥ የጌታ ቀኝ እጅ ኃይሉን አከናወነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 በጻድቃን ድንኳን የእልልታና የሆታ ድምፅ፣ እንዲህ እያለ ያስተጋባል፤ “የእግዚአብሔር ቀኝ እጅ ብርቱ ሥራ ሠራች፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 በጻድቃን ድንኳን ውስጥ እንዲህ የሚል የድል አድራጊነት ድምፅ ይሰማል፦ “የእግዚአብሔር ኀይል ያሸንፋል!”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ትእ​ዛ​ዝ​ህን አሰ​ላ​ሰ​ልሁ፥ መን​ገ​ድ​ህ​ንም እፈ​ል​ጋ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 118:15
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰሜንንና ደቡብን አንተ ፈጠርህ፥ ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል።


አቤቱ፥ የጣልኸን አንተ አይደለህምን? አምላክ ሆይ፥ ከሠራዊታችን ጋር አትወጣም።


ቀኝህ ጌታ ሆይ፥ በኃይል ታላቅ ነው፤ አቤቱ፥ ቀኝህ ጌታ ሆይ፥ ጠላትን አደቀቀ።


በክንዱ ኃያል ሥራን ሠርቶአል፤ በልባቸው የሚታበዩትን በትኖአል፤


የዳዊት መዝሙር። ለጌታ አዲስ መዝሙር ዘምሩ፥ ድንቅ ነገሮችን አድርጎአልና፥ ቀኙ፥ የተቀደሰ ክንዱም ለእርሱ ማዳን አደረገ።


“ሰማይ ሆይ! ቅዱሳን፥ ሐዋርያትና ነቢያት ሆይ! ስለተፈረደባት በእርሷ ላይ ደስ ይበላችሁ፤ እግዚአብሔር ፈርዶላችኋልና።”


ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው፤ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ።


ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ አገልጋዮቼ ይበላሉ እናንተ ግን ትራባላችሁ፤ እነሆ፥ አገልጋዮቼ ይጠጣሉ እናንተ ግን ትጠማላችሁ፤ እነሆ፥ አገልጋዮቼ ደስ ይላቸዋል እናንተ ግን ታፍራላችሁ፤


የልቤ ደስታ ነውና ምስክርህን ለዘለዓለም ወረስሁ።


ጢስ እንደሚበንን እንዲሁ ይብነኑ፥ ሰም በእሳት ፊት እንደሚቀልጥ፥ እንዲሁ ክፉዎች ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ።


እጅህ አሕዛብን አባረረች፥ እነርሱንም ተከልህ፥ አሕዛብን አስጨንቀህ እነሱን አለመለምክ።


ጻድቃን ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ፥ ልባችሁም የቀና ሁላችሁ፥ እልል በሉ።


ኃያል ሆይ፥ በግርማህና በውበትህ ሰይፍህን በወገብህ ታጠቅ።


እዚያም እናንተ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮቻችሁ፥ እንዲሁም የራሳቸው ድርሻ ወይም ርስት የሌላቸው በየከተሞቻችሁ የሚኖሩት ሌዋውያን በጌታ በአምላካችሁ ፊት ሐሤት አድርጉ።”


በእንግድነቴ አገር ሥርዓትህ መዝሙር ሆነችኝ።


በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ሐሴትን ያድርጉ፥ ለዘለዓለሙ በደስታ ይዘምሩ፥ እነርሱንም ትጠብቃቸዋለህ፥ ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይደሰቱ።


የጌታ ሥራዎች ታላላቅ ናቸው፥ ደስ በሚሰኙባቸው ሁሉ ይፈለጋሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች