Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 11:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ጌታ ጻድቅ ነውና፥ ጽድቅንም ይወድዳል፥ ቅን ሰው ፊቱን ያየዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 እግዚአብሔር ጻድቅ ነውና፤ የጽድቅ ሥራም ይወድዳል፤ ቅኖችም ፊቱን ያያሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 እግዚአብሔር ጻድቅ ስለ ሆነ የጽድቅን ሥራ ይወዳል፤ ትክክለኛ ሥራ የሚሠራ ሰው ሁሉ ፊቱን ያያል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 አቤቱ፥ አንተ ጠብ​ቀን፥ ከዚ​ህ​ችም ትው​ልድ ለዘ​ለ​ዓ​ለም ታደ​ገን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 11:7
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዓይኑን ከጻድቃን ላይ አያርቅም፥ ለዘለዓለምም ከነገሥታት ጋር በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል፥ እነርሱም ከፍ ከፍ ይላሉ።


ጌታ የዕውሮችን ዐይን ያበራል፥ ጌታ የወደቁትን ያነሣል፥ ጌታ ጻድቃንን ይወድዳል፥


እኔ ግን በጽድቅ ፊትህን አያለሁ፥ ክብርህን ሳይ እጠግባለሁ።


በማዳንህ ክብሩ ታላቅ ነው፥ ሞገስንና ግርማን በላዩ አኖርህ።


እነሆ፥ የጌታ ዐይኖች ወደሚፈሩት ናቸው፥ በቸርነቱም ወደሚታመኑ፥


ጽድቅንና ፍርድን ይወድዳል፥ የጌታ ቸርነት ምድርን ሞላች።


ከክፉ ነገር ሽሽ መልካምንም አድርግ፥ ሰላምን እሻ ተከተላትም።


ጌታ ፍርድን ይወድዳልና፥ ቅዱሳኑንም አይጥላቸውምና፥ ለዘለዓለምም ይጠብቃቸዋል ለንጹሓንም ይበቀልላቸዋል፥ የክፉዎች ዘር ግን ይጠፋል።


ይህን ሳስብ ነፍሴ በእኔ ውስጥ ፈሰሰች፥ ወደ እግዚአብሔር ቤት ወደ ምስጋና መኖሪያ ስፍራ እገባለሁና፥ በዓል የሚያከብሩ ሰዎች የደስታና ምስጋና ቃል አሰሙ።


አምላክ ሆይ፥ ዙፋንህ ለዘለዓለም ነው፥ የመንግሥትህ በትር የቅንነት በትር ነው።


ጽድቅን ወደድህ ዓመፃንም ጠላህ፥ ስለዚህ ከባልንጀሮችህ ይልቅ እግዚአብሔር አምላክ የደስታ ዘይትን ቀባህ።


በአንተ የሚታመኑት ሁሉ ሐሴትን ያድርጉ፥ ለዘለዓለሙ በደስታ ይዘምሩ፥ እነርሱንም ትጠብቃቸዋለህ፥ ስምህንም የሚወድዱ ሁሉ በአንተ ይደሰቱ።


ጋሻዬ በእግዚአብሔር ዘንድ ነው ልበ ቅኖችን የሚያድናቸው።


ጌታ በሕዝቦች ላይ ይፈርዳል፥ አቤቱ፥ እንደጽድቄ ፍረድልኝ፥ እንደ የዋህነቴም ይሁንልኝ።


ፍርድን የምትወድ ኃያል ንጉሥ፥ አንተ ቅንነትን አጸናህ፥ በያዕቆብ ፍርድንና ጽድቅን አንተ ፈጽምህ።


የኀጥኣን መንገድ በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ እርሱ ግን ጽድቅን የሚከተል ይወድዳል።


እኔ ጌታ ፍትህን የምወድ፥ ስርቆትንና በደልን የምጠላ ነኝ፤ ፍዳቸውንም በእውነት እሰጣቸዋለሁ፥ ከእነርሱም ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ።


የጌታ ዐይኖች ወደ ጻድቃን ናቸው፤ ጆሮዎቹም ለጸሎታቸው የተከፈቱ ናቸው፤ የጌታ ፊት ግን ክፉ ነገርን በሚያደርጉ ላይ ነው።”


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ቢገለጥ ግን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና።


ፊቱንም ያያሉ፤ ስሙም በግምባሮቻቸው ይኖራል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች