Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 11:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 እነሆ ክፉዎች ቀስታቸውን ገትረዋልና፥ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋልና፥ ልበ ቅኖችን በስውር ይነድፉ ዘንድ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ደግሞም ለምን እንዲህ ትሉኛላችሁ? “ክፉዎች፣ እነሆ፤ ቀስታቸውን ገትረዋል፤ የቅኑን ሰው ልብ በጨለማ ለመንደፍ፣ ፍላጻቸውን በአውታሩ ላይ ደግነዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ኃጢአተኞች በጨለማ አድብተው ልበቅኖችን ለመግደል ቀስታቸውን ገትረዋል፤ ፍላጻቸውንም በአውታር አዘጋጅተዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እርስ በር​ሳ​ቸው ከንቱ ነገ​ርን ይና​ገ​ራሉ፤ በሽ​ን​ገላ ከን​ፈር ሁለት ልብ ሆነው ይና​ገ​ራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 11:2
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።


ክፉዎች ሰይፋቸውን መዘዙ፥ ቀስታቸውንም ገተሩ ድሀውንና ችግረኛውን ይጥሉ ዘንድ፥ ልበ ቅኖችንም ይወጉ ዘንድ፥


ክፋትን በአንተ ላይ ዘርግተዋልና፥ የማይቻላቸውንም ምክር አሰቡ።


ኢየሱስን በተንኰል ይዘው ሊገድሉት ተማከሩ፤


ሮሮዬን በፊቱ አፈስሳለሁ፥ መከራዬንም በፊቱ እናገራለሁ።


አቤቱ፥ ለመልካሞች፥ ልባቸውም ለቀና መልካምን አድርግ።


ብርሃን ለጻድቃን፥ ደስታም ለልበ ቅኖች ወጣ።


ፍርድ ወደ ጽድቅ እስክትመለስ ድረስ ልበ ቅኖችም ሁሉ ይከተሉአታል።


ሰዎች ሁሉ ፈሩ፥ የእግዚአብሔርንም ሥራ ተናገሩ፥ ሥራውንም አስተዋሉ።


ጻድቃን ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ ሐሤትም አድርጉ፥ ልባችሁም የቀና ሁላችሁ፥ እልል በሉ።


በክፉዎች ትዕቢት ምስኪኖች ይሰደዳሉ፥ ባሰቡት ተንኰላቸው ተጠመዱ።


እግዚአብሔር ጻድቅ ዳኛ ነው፥ ሁልጊዜ ትክክለኛ ፈራጅ ነው፥


የክፉዎች በደል ይጥፋ፥ ጻድቁን ግን አቅና፥ እግዚአብሔር ልብንና ኩላሊትን ይመረምራል።


ዳዊትም ሳኦል ክፉ እንዳሰበበት ባወቀ ጊዜ፥ ካህኑን አብያታርን፥ “ኤፉዱን አምጣ” አለው።


ሳኦልም በልቡ፥ “ወጥመድ እንድትሆነው፥ በፍልስጥኤማውያንም እጅ እንዲጠፋ እርሷን እድርለታለሁ” ሲል አሰበ። ስለዚህ ሳኦል ለሁለተኛ ጊዜ ዳዊትን፥ “እነሆ፤ ዛሬ ዐማቼ ትሆናለህ” አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች