26 አቤቱ አምላኬ፥ እርዳኝ፥ እንደ ጽኑ ፍቅርህም አድነኝ።
26 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ፤ ርዳኝ፤ እንደ ምሕረትህም አድነኝ።
26 እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! እባክህ እርዳኝ፤ ስለ ዘለዓለማዊው ፍቅርህም አድነኝ።
ትእዛዛትህ ሁሉ እውነት ናቸው፥ በዓመፅ አሳድደውኛል፥ እርዳኝ።
እርሱም ሥጋ ለብሶ በምድር በሚመላለስ ጊዜ፥ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል፥ ከብርቱ ጩኸትና ከእንባ ጋር ጸሎትንና ምልጃን አቀረበ፤ ስለ ጻድቅ ፍርሃቱም ጸሎቱ ተሰማለት፤
በደጅ የሚቀመጡ በእኔ ይጫወታሉ፥ ሰካራሞች በእኔ ላይ ይዘፍናሉ።
ለመዘምራን አለቃ፥ አታጥፋ። ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ፥ የዳዊት ቅኔ።
የውኃው ማዕበል አያስጥመኝ፥ ጥልቁም አይዋጠኝ፥ ጉድጓድም አፉን በእኔ ላይ አይዝጋ።
አቤቱ፥ አንተ ርኅራኄህን ከእኔ አታርቅ፥ ቸርነትህና እውነትህ ዘወትር ይጠብቁኝ።