Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 109:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 የክፉና የተንኰለኛ አፎች በላዬ ተላቅቀውብኛልና፥ በሐሰት አንደበትም በላዬ ተናገሩ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ክፉዎችና አታላዮች፣ አፋቸውን ከፍተውብኛልና፤ በውሸተኛ አንደበት ተናግረውብኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ክፉዎችና ሐሰተኞች ተቃውመውኛል፤ በእኔ ላይ በሐሰት ይናገራሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የኀ​ይ​ልን በትር ከጽ​ዮን ይል​ክ​ል​ሃል፤ በጠ​ላ​ቶ​ች​ህም መካ​ከል ትገ​ዛ​ለህ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 109:2
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አንደበትህ ጥፋትን ያስባል፥ እንደ ተሳለ ምላጭ ሽንገላን አደረግህ።


ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ያታልላል በእውነትም አይናገሩም፤ ሐሰትን መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፥ ክፉንም ለማድረግ ይደክማሉ።


ትዕቢተኛ ዐይን፥ ሐሰተኛ ምላስ፥ ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥


“ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤


የእውነት ከንፈር ለዘለዓለም ትቆማለች፥ ውሸተኛ ምላስ ግን ለቅጽበት ነው።


አቤቱ፥ አንተን ጠርቻለሁና አልፈር፥ ክፉዎች ይፈሩ በሲኦልም ዝም ይበሉ።


እንደ ሞተ ሰው ከልብ ተረሳሁ፥ እንደ ተበላሸ ዕቃም ሆንሁ።


አኪጦፌልም፥ አቤሴሎምን እንዲህ አለው፤ “ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰው ልምረጥና፥ ዛሬ ሌሊት ተነሥቼ ዳዊትን አሳድደዋለሁ፤


ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።


የጻድቅ ልብ መልሱን ያስባል፥ የኀጥኣን አፍ ግን ክፋትን ያፈልቃል።


በልባቸውም ክፉ ካሰቡ፥ ቀኑን ሁሉ ለሰልፍ ከሚከማቹ።


ከዕብራውያን ምድር ወደዚህ የመጣሁት በአፈና ነው፤ አሁንም ቢሆን እዚህ እስር ቤት የተጣልሁት አንዳች ጥፋት ኖሮብኝ አይደለም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች