29 ዐውሎ ነፋሱን አስቆመ፥ ሞገዱም ጸጥ አለ።
29 ዐውሎ ነፋሱን ጸጥ አደረገ፤ የባሕሩም ሞገድ ረጭ አለ።
29 ዐውሎ ነፋሱንና ማዕበሉን ጸጥ አደረገ።
እርሱም “እናንተ እምነት የጎደላችሁ! ለምን ትፈራላችሁ?” አላቸው፤ ከዚህ በኋላ ተነሥቶ ነፋሱንና ባሕሩን ገሠጸው፤ ታላቅ ጸጥታም ሆነ።
በጉልበትህ ተራሮችን አጸናሃቸው፥ በኃይልም ታጥቀሃል።
አቤቱ የሠራዊት አምላክ፥ እንደ አንተ ያለ ማን ነው? አቤቱ፥ አንተ ብርቱ ነህ፥ እውነትህም ይከብብሃል።
ዮናስንም አንሥተው ወደ ባሕሩ ጣሉት፤ ባሕሩም መናወጡን አቆመ።
የባሕሩን ማጓራት፥ የሞገድንም ጩኸት፥ የአሕዛብንም ማጉረምረም ዝም ታሰኛለህ።